avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
25.01.2026 02:32
ዋዜማ ሬዲዮ “ፍቃዱን” የመለሰው በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በተሰጠው “ትዕዛዝ” መሆኑን ገለጸ

በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን እገዳ የታጠለበት ዋዜማ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን፤ የተወሰደበት እርምጃ “በማንኛውም መመዘኛ ትክክል ነው” ብሎ እንደማያምን ገለጸ።

መገናኛ ብዙሃኑ ከባለስልጣኑ የተሰጠውን “ፍቃድ” የመለሰው፤ ከትላንት በስቲያ ሐሙስ ከመስሪያ ቤቱ በደረሰው ትዕዛዝ መሰረት መሆኑን አስታውቋል።

“ዋዜማ ሬድዮ” በሚል ስያሜ በስደት ላይ በነበሩ ሶስት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች በሰኔ 2006 ዓ.ም የተቋቋመው መገናኛ ብዙሃኑ፤ “በኢትዮጵያ ያለውን የስራ ፍቃድ” ተመላሽ ያደረገው ዛሬ ቅዳሜ ጥር 16፤ 2018 ነው።

መገናኛ ብዙሃኑ “የስራ ፈቃድ እውቅናውን” የመለሰው፤ የኢትዮጵያን ህገ-መንግስት፣ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅን፣ መመሪያዎችን እና የሙያ ስነምግባርን “አክብሮ ለመስራት” “ፈቃደኛ ባለመሆኑ” ምክንያት እንደሆነ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ወንጅሏል።

የመገናኛ ብዙሃኑ ዘገባዎች የኢትዮጵያን “ብሔራዊ ጥቅም የሚጻረሩ”፣ “ሚዛናዊነት የሚጎድላቸው” እና “የሙያ ስነምግባርን የጣሱ” “የአንድ ወገን ዘገባ ብቻ” የተንጸባረቁባቸው ሆነው መገኘታቸውንም ባለስልጣኑ በመግለጫው ላይ ጠቅሷል።

የዋዜማ መገናኛ ብዙሃን አመራር ምሽቱን ባወጣው መግለጫ፤ ባለስልጣኑ ያቀረባቸውን “ክሶች” “የኢትዮጵያን ሚዲያ ለሚከታተሉ ተደራሲዎች፣ ታዛቢዎች እና ባለሞያዎች የሕሊና ፍርድ እንተዋለን” ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

🔴ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17231/

@EthiopiaInsiderNews
18
👍 5
🤬 2
4 7.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram