avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
24.01.2026 21:35
በጋምቤላ ከተማ ከነገ በስቲያ ሰኞ ጀምሮ በትምህርት ገበታቸው ላይ የማይገኙ ተማሪዎች፤ ለአንደኛ ወሰነ ትምህርት (ሴሚስተር) ማጠቃለያ ፈተና መቀመጥ እንደማይችሉ የከተማይቱ ትምህርት ጽህፈት ቤት አስጠነቀቀ።

በከተማይቱ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የመማር ማስተማር ሂደታቸውን ካቋረጡ ትምህርት ቤቶች መካከል አምስቱ አሁንም ትምህርት አለመጀመራቸውን ጽህፈት ቤቱ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጿል።

የጋምቤላ ክልል መንግስት መቀመጫ በሆነችው የጋምቤላ ክልል 14 የመንግስት አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ። በከተማይቱ ካለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ጀምሮ በተከሰተ “የጸጥታ መደፍረስ” እና “ግጭት” ምክንያት ለአንድ ወር ያህል ትምህርት ቤቶች ዝግ ሆነው ቆይተዋል።

በጋምቤላ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ያለው የጸጥታ ሁኔታ መሻሻሉን ተከትሎ፤ ተቋርጦ የነበረው መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ከታህሳስ 27፤ 2018 ጀምሮ ወደነበረበት እንዲመለስ የክልሉ ትምህርት ቤት ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።

በተመሳሳይ መልኩ በጋምቤላ ከተማ “በተፈጠረው አንጻራዊ ሰላም” የመማር ማስተማር ሂደቱ ወደ ቀድሞ ሁኔታው እንዲመለስ መግባባት ላይ ተደርሶ እንደነበር የከተማይቱ ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ኡሞድ ኡፖዲ፤ በጋምቤላ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምህርት መልሶ እንዲጀመር ውሳኔ የተላለፈው ከሁለት ሳምንት በፊት እንደነበር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ይህን ተከትሎም በግል ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደቱ መጀመሩን ኃላፊው ገልጸዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17226/

@EthiopiaInsiderNews
8
👎 2
3 7.5K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram