ኢትዮጵያ የራሷን ጥቅም “በየዋህነት፣ በተላላ፣ በአጭር ጊዜ ድል” አሳልፋ እንደማትሰጥ፤ የተሰጠ ካለም “ማወራረዷን እንደማትተው” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ቀጣዩ ዐቢይ ተግባር” የኢትዮጵያን “ስትራቴጂክ ፍላጎት” እና “ብሔራዊ ጥቅም” ማረጋገጥ መሆኑንም አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የኢፌዲሪ አየር ኃይል 90ኛ ዓመት ምስረታን አስመልክቶ፤ ቢሾፍቱ በሚገኘው የተቋሙ ዋና ቅጽር ግቢ በተዘጋጀ ክብረ በዓል ላይ ዛሬ ቅዳሜ ጥር 16፤ 2018 ባደረጉት ንግግር ነው።
የኢፌዲሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የሆኑት አብይ በዚሁ ንግግራቸው፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ላለፉት ዘጠኝ አስርት ዓመታት “በብዙ ከፍታ”፣ “በብዙ ዝቅታ” ውስጥ ማለፉን አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይልን “ስመጥር” እና “ታላቅ” ሲሉ ያሞካሹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ተቋሙ አሁን ያለበት ቁመና በየዘመናቱ የነበሩ መንግስታት የሰሯቸው “ድምር ስራዎች ውጤት” እንደሆነ ገልጸዋል።
አየር ኃይሉ አሁን ያለበት ደረጃ፤ “ላለፉት 90 ዓመታት ከነበረበት “ከፍ ያለ” እና “የላቀ ብቃት የያዘበት ጊዜ” እንደሆነ “በድፍረት መናገር” እንደሚቻልም ጠቁመዋል።
“በአየር ኃይል መብቃት፣ ማሳደግ የሚያስፈልግበት ዋናው ምክንያት በስጋ እና በአጥንት ድል ማስመዝገብ ያደረ፣ የቀረ ስርዓት ስለሆነ [ነው]። በተኩስ አቅም፣ ኢላማን በትክክል በመምታት (precision)፤ ብዙ ምሽጎች ማፍረስ እና ውጊያን ማሳጠር ታሳቢ ያደረገ አቅጣጫን እንከተላለን” ብለዋል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዡ።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17221/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram