በመጪው ሀገር አቀፍ ምርጫ ለውድድር የሚቀርቡ ዕጩዎችን ለመመዝገብ የተዘጋጀው የዲጂታል ስርዓት፤ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን “ከፉክክር ሜዳው በማውጣት ህዝብን አማራጭ አሳጥቶ ለመግዛት የታሰበ የፖለቲካ ሴራ ነው” የሚል ነቀፋ ቀረበበት።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ፤ የምርጫ ሂደቱን “ለመጉዳት” በመስሪያ ቤቱ “ሆን ተብሎ የሚደረግ ተግባር የለም” ሲል አስተባብሏል።
ዛሬ አርብ ጥር 15፤ 2018 ባወጡት የጋራ መግለጫ፤ በዲጂታል ሥርዓቱ እና በምርጫ ቦርድ የዕጩዎች ምዝገባ መስፈርቶች ላይ ተቃውሞ ያቀረቡት ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች እና አንድ የፓርቲዎች ስብስብ ናቸው።
ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በዚሁ መግለጫቸው “ግልጽነት በጎደለው” እና “በተድበሰበሰ የምዝገባ አሠራርና ሂደት”፤ በመጪው ግንቦት መጨረሻ የሚካሄደው ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ “አሳታፊ፣ ሃቀኛ፣ ተዓማኒ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ሊሆን አይችልም” ሲሉም አቋማቸውን አስታውቀዋል።
ሀገር አቀፉ ምርጫ ሊካሄድ ወራት በቀሩበት በአሁኑ ወቅት፤ በዕጩዎች ምዝገባ ጅማሮ ላይ “በርካታ ተግዳሮቶች አጋጥመውናል” ብለዋል ፓርቲዎቹ።
ከቅሬታ አቅራቢ ፓርቲዎች አንዱ የሆነው የኢሕአፓ ፕሬዝዳንት አቶ አብርሃም ኃይማኖት፤ በዲጂታሉ አማራጭ አንድ ዕጩ መታወቂያው ከተመዘገበበት አካባቢ ውጭ ባለ የምርጫ ክልል ለተወዳዳሪነት የመመዝገብ ዕድል እንደሌለው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ማስተባበርያ ክፍል ኃላፊ ቀነኒ እንሰርሙ፤ የዕጩዎች የሰነድ ማረጋገጫ በልደት ሰርተፍኬት እና በመታወቂያ ላይ ብቻ የተመሰረተ እንዳልሆነ ምላሽ ሰጥተዋል።
🔴ለዝርዝሩ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17213/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram