የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳው ኢትዮጵያን ጨምሮ በአራት የአፍሪካ ሀገራት ከነገ ጀምሮ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።
ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ጨምሮ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር “በቀጠናዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች” ላይ እንደሚወያዩ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል።
ምክትል ሚኒስትሩ በዚሁ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ወደ ግብጽ፣ ኬንያ እና ጅቡቲ ይጓዛሉ።
የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመጋቢት 2017 ዓ.ም የተሾሙት ክሪስቶፈር ላንዳው፤ ወደ ካይሮ እና አዲስ አበባ የሚጓዙት የሀገራቸው ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያ እና ግብጽ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ምክንያት የገቡበትን ውዝግብ ለመፍታት እንደሚሹ ባስታወቁ በጥቂት ቀናት ውስጥ ነው።
የላንዳው የመጀመሪያ መዳረሻ በሆነችው ግብጽ፤ ላንዳው “በአካባቢያዊ ተግዳሮቶች” ላይ ስለሚደረግ ትብብር ከሀገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚወያዩ መስሪያ ቤታቸው ገልጿል።
በእነዚህ ውይይቶች የአሜሪካ እና የግብጽ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነትን ማጠናከርን የተመለከቱ ጉዳዮች እንደሚነሱም መስሪያ ቤቱ አመልክቷል።
የአሜሪካው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከካይሮ ወደ አዲስ አበባ ሲያቀኑ፤ በዩናይትድ ስቴትስ ጦር የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን አብረዋቸው ይጓዛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን ባለፈው ህዳር በአዲስ አበባ ተገናኝተው ነበር።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17207/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram