avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
23.01.2026 18:04
ከ20 ዓመት በላይ በሥራ ላይ የቆየውን “የኢትዮጵያ አቪዬሽን ደህንነት አዋጅ” የሚያሻሻል የአዋጅ ረቂቅ፤ ትላንት ሐሙስ ጥር 14፣ 2018 በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ቀርቧል።

የአዋጅ ረቂቁ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የፓርላማው ቋሚ ኮሚቴዎች የተመራው፤ ውይይት ሳይካሄድበት እና አስተያየትም ሆነ ጥያቄ ሳይቀርብበት ነው።

የህግ ረቂቁ በነባሩ አዋጅ ውስጥ ያልተካተቱ አዳዲስ ድንጋጌዎችን አካትቷል። አዲሱ አዋጅ በዋናነት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሥልጣን እና ተግባራት ላይ ማሻሻያዎችን አድርጓል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የጉምሩክ ኮሚሽን ተጨማሪ ሥልጣን እና ተግባር በማሻሻያ አዋጁ ተሰጥቷቸዋል።

የአዋጅ ረቂቁ የአቪዬሽን ደህንነት አገልግሎት ክፍያ እና የመንገደኞች ፍተሻን በተመለከተም አዳዲስ ድንጋጌዎች አካትቷል።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በአዲሱ አዋጅ የተሻሻሉትን እና አዲስ የተካተቱትን ድንጋጌዎችን በዝርዝር አጠናቅራለች።

🔴ዝርዝር ጥንቅሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17199/

@EthiopiaInsiderNews
5
4 6.2K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram