avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
23.01.2026 01:45
በጋምቤላ ከተማ ከነገ ጀምሮ “ላልተወሰነ ጊዜ” ሞተር ሳይክል ማሽከርከር ተከለከለ

በጋምቤላ ከተማ ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት፤ ከነገ አርብ ጥር 15፤ 2018 ጀምሮ የመንግስትም ሆነ የግል ሞተር ሳይክሎች “ላልተወሰነ ጊዜ” ማሽከርከር “በጥብቅ የተከለከለ” መሆኑን የከተማይቱ አስተዳደር አስታወቀ።

በከተማው የሚገኙ ሆቴሎች እና ግሮሰሪዎችም አገልግሎት መስጠት የሚችሉት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ ብቻ መሆኑን አስተዳደሩ ገልጿል።

አስተዳደሩ ይህን የገለጸው በጋምቤላ ከተማ ባለው “ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ” ላይ ከተወያየ በኋላ መሆኑን የከተማይቱ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ምሽቱን ባወጣው መግለጫ ላይ አመልክቷል።

የከተማ አስተዳደሩ ከውይይቱ በኋላ ባሳለፈው ውሳኔ ከሞተር ሳይክል ክልከላ በተጨማሪ በከተማው የሚገኙ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጆች) አገልግሎት መስጠት በሚችሉበት ጊዜ ላይም ገደብ ጥሏል።

በውሳኔው መሰረት በጋምቤላ ከተማ የሚገኙ ባጃጆች አገልግሎት መስጠት የሚችሉት ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ ምሽት 1 ሰዓት ብቻ ነው። እነዚህን ክልከላዎች እና ገደቦች ጥሶ በተገኘ “ማንኛውም ግለሰብ” ላይ “አስተዳደራዊ እርምጃ” የሚወሰድበት መሆኑንም የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር በዛሬ መግለጫው አስጠንቅቋል።

🔴ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17196/

@EthiopiaInsiderNews
👍 10
2
8 7.2K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram