avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
22.01.2026 21:16
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፓርላማ ተመራጩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ ኢትዮጵያ እና ቻይና የደረሱበት አይነት የሁለትዮሽ ስምምነቶች “የሀገሪቱን ብሔራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ይጎዳል” የሚል ግምገማ እንዳላቸው ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት ገልጸዋል።

ቻይናውያን ዜጎች “በተለይ እና በተደጋጋሚ” የሚሳተፉባቸው በሚዲያ የሚሰሙ “የታወቁ ወንጀሎች” መኖራቸውን ያነሱት የፓርላማ አባሉ፤ ወንጀሎቹ በከፍተኛ ሁኔታ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ጥቅም የሚጎዱ እንደሆኑ አስረድተዋል።

ዶ/ር ደሳለኝ ቻይናውያን “ጎላ ብለው የሚታዩባቸው” በማለት የጠቀሷቸው ወንጀሎች “ህገወጥ የማዕድን ማውጣት እና ማዘወዋር” እንዲሁም “በህገ ወጥ የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ” (money laundering) ናቸው።

በእንደዚህ አይነት ወንጀሎች የሚሳተፉ ዜጎች በኢትዮጵያ የህግ ስነ ስርዓት “እዚሁ የፍርድ ሂደታቸውን ማጠናቀቅ አለባቸው” ብለው እንደሚያምኑ የገለጹት የፓርላማ አባሉ፤ ግለሰቦቹ ተፈርዶባቸው ወደ ሀገራቸው ከተላለፉ በኋላ “ፍርዱ እዚያ ስለመፈጸሙ ምን ቁጥጥር አለን?” ሲሉ ጠይቀዋል።

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የፓርላማው የህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ አዋጁ “ፍርደኞች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ይለቀቃሉ” የሚል አንደምታ እንደሌለው አንስተዋል።

ፍርደኞችን ለመለዋወጥ ሕጋዊ ስምምነት ያስፈለገው “ለአሰራር ምቾት” በማሰብ እንጂ አስቀድሞም በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እስረኞችን የማስተላለፍ ስራ ሲከናወን እንደነበረ አስታውሰዋል።

🔴ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17183/

🔴በቪዲዮ ለመመልከት ➡️ https://youtu.be/0q3UIMjgxGE

@EthiopiaInsiderNews
16
👏 2
🤔 2
👎 1
7 6.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram