avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
22.01.2026 00:43
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና የግብጹን ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲን ማገናኘት እንደሚፈልጉ ተናገሩ።

ትራምፕ ሁለቱን መሪዎች ማገናኘት የሚፈልጉት፤ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ምክንያት በኢትዮጵያ እና በግብጽ መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ የሚፈታ ስምምነት ለማበጀት እንደሆነ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት፤ በስዊትዘርላንድ ዳቮስ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን ከግብጹ አቻቸው ጋር ተገናኝተው በተወያዩበት ወቅት ነው።

ዛሬ ረቡዕ ምሽት በተካሄደው በሁለቱ ፕሬዝዳንቶች ውይይት ላይ፤ የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና የግብጽ አቻቸው ባድር አብደላቲን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

ትራምፕ ውይይቱን ሲጀመሩ “ከግብጽ ጋር በጣም ጥሩ ግንኙነት አለን። ፕሬዝዳንቱ ደውለው አንዳች ነገር ይጠይቃሉ። ሁል ጊዜም መፍትሔ እናገኝለታለን” ሲሉ ተደምጠዋል።

አልሲሲ በፊናቸው “የህልውና ጉዳይ” ያሉትን የናይል ወንዝን እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ በተመለከተ ትራምፕ ለሀገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ አመስግነዋል።

በትራምፕ የመጀመሪያ የስልጣን ዘመን በግድቡ ጉዳይ ላይ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ እንደነበር ያስታወሱት አልሲሲ፤ በወቅቱ ተዘጋጅቶ የነበረው ስምምነት እንዲፈረም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት “ሁሉንም ነገር” ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።


ፕሬዝዳንት ትራምፕም በምላሻቸው የታላቁ ህዳሴን ግድብ ጉዳይ ቅድሚያ ሰጥተው ተናግረዋል። ትራምፕ በዚሁ ንግግራቸው የህዳሴውን ግድብ ከዓለም ግዙፍ ግድቦች አንዱ እንደሆነ ጠቅሰው፤ የግንባታ ወጪውን የሸፈነችው ሀገራቸው እንደሆነች ተናግረዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17167/

@EthiopiaInsiderNews
😁 28
17
👎 3
👍 2
👏 1
🤔 1
5 6.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram