በዜጎች “ደህንነት”፣ “ሰላም” እና “ጤና” ላይ “ከፍተኛ ተጽዕኖ” የሚያስከትል አደጋ “እንደሚከሰት ሲታመን”፤ ማንኛውም የስፖርት ኩነት እንዳይካሄድ ለማገድ የሚያስችል የአዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ሊቀርብ ነው።
ስፖርታዊ ዝግጅቶች ከመጀመራቸው በፊትም ሆነ በሚካሄዱበት ወቅት “ማንኛውንም አይነት የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን” ማካሄድ እንደማይቻልም የአዋጅ ረቂቁ ይከለክላል።
“የፌደራል የስፖርት ልማት እና አስተዳደር አዋጅ” የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የአዋጅ ረቂቅ፤ ነገ ሐሙስ ጥር 14፤ 2018 በሚካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ እንዲቀርብ አጀንዳ ተይዞለታል።
በዚህ የአዋጅ ረቂቅ ላይ የተወያየው የሚኒስትሮች ምክር ቤት፤ ግብአቶችን በማከል ወደ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ የወሰነው ከሁለት ሳምንት በፊት ነበር።
በ70 አንቀጾች የተከፋፈለው ይህ አዋጅ በውስጡ ከያዛቸው ክፍሎች ውስጥ የስፖርት ተቋማትን ስለማቋቋም እና ስለማስተዳደር፣ የስፖርት ፋይናንስ አስተዳደር እንዲሁም የስፖርት ግጭት አፈታት ስርዓትን የተመለከቱት ይገኙበታል።
የስፖርት ኩነቶች አስተዳደር እና የሽልማት አሰጣጥ ስርዓትን የተመለከቱ ዝርዝር ድንጋጌዎችም በአዋጁ ረቂቁ ተካትተዋል።
የአዋጅ ረቂቁ “የስፖርት ኩነቶችን ማገድ” የሚቻልበትን ድንጋጌም በውስጡ አካትቷል።
እገዳውን የሚጥለው የስፖርት እና ባህል ሚኒስቴር “ከመንግስት አካል ሪፖርት ሲደርሰው” መሆኑም በአዋጁ ረቂቁ ላይ ተመልክቷል። ሆኖም ረቂቅ ህጉ “የመንግስት አካል” የተባለው የትኛው ተቋም ወይም መስሪያ ቤት እንደሆነ በግልጽ አላሳወቀም።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17157/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram