avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
20.01.2026 20:47
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባካሔደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፤ የባንኮች ፍላጎት ከአቅርቦት በ24.7 ሚሊዮን ዶላር በለጠ። ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት ባካሄደው የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ከተሳተፉ 21 ባንኮች መካከል ስድስቱ ዶላር ሳያገኙ ቀርተዋል።

ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንት ልዩነት “መደበኛ እና “ተከታታይ” የውጭ ምንዛሬ ሽያጭ ጨረታ ማካሄድ የጀመረው ከመጋቢት 2017 ዓ.ም መጨረሻ አንስቶ ነው። በዚህም መሰረት ባንኩ 15ኛውን ዙር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ፤ ዛሬ ማክሰኞ ጥር 12፤ 2018 አካሄዷል።

በዚሁ ጨረታ ማዕከላዊው ባንክ ለጨረታ ያቀረበው 70 ሚሊዮን ዶላር ቢሆንም፤ በጨረታው የተሳተፉ ባንኮች ባቀረቡት ዋጋ የተጠየቀው አጠቃላይ የውጭ ምንዛሬ መጠን ግን 94.7 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ብሔራዊ ባንክ ይፋ ያደረገው የውጤት መግለጫ ያሳያል።

ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም የውጭ ምንዛሬ ጨረታዎች ካካሔደ በኋላ አማካኝ ጭማቂ ዋጋ እና የተሳታፊ ባንኮችን ቁጥር ብቻ ይፋ ሲያደርግ ቆይቷል። ጨረታዎቹን በቅርበት የሚከታተሉ የባንክ እና የፋይናንስ ባለሙያዎች፤ ማዕከላዊው ባንክ ውጤቶችን ይፋ ሲያደርግ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች እንዲያቀርብ ሲወተውቱ ቆይተዋል።

ባንኩ በዛሬው የጨረታ ውጤት ተጨማሪ መረጃዎችን ማካተቱ፤ “የውጭ ምንዛሬ ስርዓትን ለማረጋጋት ያግዛል” ከሚል ዕሳቤ የመነጨ ሊሆን እንደሚችል አንድ የፋይናንስ ባለሙያ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17145/

@EthiopiaInsiderNews
8
🤔 2
5 6.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram