በግብጽ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የአባይን “ውሃ የመጋራት” ጥያቄ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ “በኃላፊነት ለመፍታት”፤ የአሜሪካንን ሽምግልና ዳግም ለማስጀመር ዝግጁ መሆናቸውን የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገለጹ።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያለውን ውጥረት መፍታትን ቅድሚያ የሰጡት፤ በግብጽ እና በኢትዮጵያ መካከል “ከፍተኛ ወታደራዊ ግጭት” እንዳይቀሰቀስ “ለመከላከል” እንደሆነ በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ አስታውቀዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የህዳሴውን ግድብ ድርድር እንደገና ለማስጀመር መዘጋጀታቸውን የገለጹት፤ ለግብጹ አቻቸው አብዱል ፋታህ አልሲሲ ትላንት አርብ ጥር 8፤ 2018 በጻፉት ደብዳቤ ነው።
የፕሬዝዳንቱ ደብዳቤ በቅደም ተከተል ለሳዑዲ አረቢያው ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን፣ ለተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝደንት ሼኽ ሞሐመድ ቢን ዛይድ አልናህያን፣ ለኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እና ለሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር አብደል-ፋታህ አል-ቡርሃን ግልባጭ ተደርጓል።
ትራምፕ ለአልሲሲ በጻፉት ደብዳቤ፤ “በግል ጓደኝነታቸው” እና አሜሪካ “ለግብጽ ህዝብ ሰላም እና ደህንነት ባላት ቁርጠኝነት መንፈስ” በኢትዮጵያ እና የግብጽ መካከል የሚካሄድን ድርድር ዳግም ለማስጀመር ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
የአሜሪካ ሽምግልና በግብጽ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የአባይን “ውሃ የመጋራት” ጥያቄ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ “በኃላፊነት ለመፍታት” የሚደረግ እንደሚሆንም አመልክተዋል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17137/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram