ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በተለያዩ የዓለም አካባቢዎች ያሉ “መናጦች” እና “መታወኮችን” ባትፈልግም፤ ከእያንዳንዱ ግጭት “ዕድል ፈልቅቃ ማውጣት” እንደሚጠበቅባት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ።
ዓለም ባልተናጠችበት ወቅት “ጥቅም አግኝተን፣ ስትናጥ እንደምንጎዳ [በማሰብ] ከእነሱ በላይ መጨነቅ የለብንም” ሲሉም ተደምጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት “የፋይናንስ እመርታ በኢትዮጵያ” በተሰኘ ኮንፍረንስ ላይ ከታደሙ ተሳታፊዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ ነው።
በኮንፍረንሱ ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጥያቄ ካቀረቡ ተሳታፊዎች መካከል የሲቢኢ የካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ይገኙበታል።
በዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አማካሪነታቸው ይበልጥኑ የሚታወቁት የአቶ ዘመዴነህ ጥያቄ፤ ተነባቢው የአሜሪካው “ኒውዮርክ ታይምስ” ጋዜጣ ከቀናት በፊት በአስተያየት አምዱ ላይ ባወጣው ጹሁፍ ላይ የተንተራሰ ነበር።
የደቡባዊ ዓለም ሀገራትን ጉዳይ ያነሱት አቶ ዘመዴነህ፤ ኢትዮጵያ ወደ አንድ አቅጣጫ የመወገን አካሄድ ባትከትልም ከአሜሪካ በኩል ግፊት እንዳለ አመልክተዋል።
“ኢትዮጵያ ከምዕራባውያንም፣ ከምስራቁም ከሁሉም ጋር ወዳጅነት አላት። ግን ‘አንዱን ወገን ምረጡ’ የሚል አቋም እየተወሰደ ነው። በተለይ ከዋሽንግተን የሚመጣው። ከማን ጋር የንግድ ልውውጥ እንደምናደርግ፣ ከማን ጋር ኢንቬስት እንደምናደርግ እየተነገረን ነው። መሀል እንድንቀመጥ የሚፈቅድሉን አልመሰለኝም” ሲሉ አቶ ዘመዴነህ የጥያቄያቸውን መንደርደሪያ አሰምተዋል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17129/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram