የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉን አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በእነ ዮሃንስ ቧያለው መዝገብ ስር የሽብር ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች፤ በግል ስልካቸው ያደረጓቸው የድምጽ ልውውጦች “ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መጠለፉን” ጉዳያቸውን ለሚመለከተው ችሎት አስታወቁ።
ተከሳሾቹ በዐቃቤ ሕግ በማስረጃነት የቀረበው የድምጽ ልውውጥ በህጉ መሰረት ስለመፈጸሙ እንዲረጋገጥላቸው አቤት ብለዋል።
በአማራ ክልል ካለው የጸጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ በእነ አቶ ዮሃንስ ቧያለው መዝገብ ስር የሽብር ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች ብዛት 52 ተከሳሾች ነው።
ዐቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የመሰረተውን የሽብር ክስ ያስረዱልኛል በሚል የሰው ምስክሮች፣ የሰነድ ማስረጃ፣ የቪዲዮ፣ ኦዲዮ እና ሰነድ ማስረጃዎችን በፍላሽ ያካተተ “ገላጭ” እንዲሁም “የኤግዚቢት“ ማስረጃዎችን ጉዳዩን ለሚመለከተው ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት አቅርቧል።
በተከሳሾቹ ላይ የቀረቡ የሰው ምስክሮችን ቃል አዳምጦ የጨረሰው ችሎቱ፤ ዐቃቤ ሕግ ባቀረባቸው በሰነድ ማስረጃዎች ላይ ተጠርጣሪዎቹ አስተያየት እንዲሰጡ ለዛሬ አርብ ጥር 8፤ 2018 ቀጥሮ ሰጥቶ ነበር።
ዐቃቤ ሕግ በማስረጃነት ካቀረባቸው መካከል የተከሳሾች የስልክ ልውውጥ እንደሚገኝበት የጠቀሱት ተከሳሾቹ፤ የዜጎችን የግል ስልክ ልውውጥ መጥለፍ የሚቻለው በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ብቻ መሆኑን ለችሎቱ ገልጸዋል።
ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው የክስ ፋይል ላይ፤ በማስረጃነት የተያያዘው የተከሳሾች የስልክ ግንኙነት ጠለፋ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎትን በማስፈቀድ የተደረገ መሆኑን አመልክቷል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17119/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram