የትግራይ እና የአማራ ክልሎች በሚወዛገቡበት የወልቃይት አካባቢ የሚኖረው ህዝብ፤ “በተገቢው ጊዜ” “የፖለቲካ እጣ ፈንታውን እንዲወስን” ሊደረግ እንደሚገባ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ አሳሰቡ።
የአካባቢዎች ነዋሪዎችን የወደፊት የኑሮ ሁኔታ በተመለከተ፤ አሜሪካ “በኢትዮጵያ የሚመራ” እና “በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እገዛ የሚደረግለትን” ሂደት እንደምትደግፍም ገልጸዋል።
አምባሳደር ማሲንጋ ይህን ያሉት፤ ዛሬ ሐሙስ ጥር 7፤ 2018 ዓ.ም በሁመራ ያደረጉትን ጉብኝት በተመለከተ ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
ማሲንጋ በዚሁ መልዕክታቸው በሁመራ በነበራቸው ቆይታ፤ በአካባቢው ያለው ህዝብ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች በአይናቸው መመልከታቸውን ገልጸዋል።
በአካባቢው ባሉ መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት መድረሱን፣ የሕክምና አገልግሎቶች የተገደቡ መሆናቸውን እና የመሠረታዊ አገልግሎቶች እጥረት መኖሩን አምባሳደሩ በመልዕክታቸው ዘርዝረዋል።
እነዚህ ተግዳሮቶች በብዙዎች ሕይወት ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ መቀጠሉን የገለጹት ማሲንጋ፤ እነዚህን ችግሮች በአስቸኳይ እንዲስተካከሉ በህዝቡ ዘንድ ያለውን ፍላጎት ጠቁመዋል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17112/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram