አዲስ አበባ 46ኛ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ልታገኝ ነው
ለአዲስ አበባ ከተማ በአሁኑ ወቅት አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙ 45 የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያዎች ተጨማሪ የሆነ ጣቢያ ግንባታ ከትላንት በስቲያ መጀመሩን የከተማይቱ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን አስታወቀ።
ጣቢያው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉትን የካ፣ ቦሌ እና ለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።
አዲሱ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ የሚገነባበት ስፍራ፤ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 “ጎሮ” በሚባለው አካባቢ የሚገኝ ነው።
“ሲጂሲ ኦሲ” በተባለው ስራ ተቋራጭ ኩባንያ የሚገነባው ይህ ጣቢያ፤ በቀን 52 ሺህ ሜትር ኪዩብ ወይም 52 ሚሊዮን ሊትር ፍሳሽ ቆሻሻን የማጣራት አቅም ይኖረዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ መገንባት ካስፈለገባቸው ምክንያቶች አንዱ፤ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ማጣሪያዎች በቂ ባለመሆናቸው ምክንያት እንደሆነ የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
ለዚህም ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከጎሮው የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ በተጨማሪ በቦሌ ክፍለ ከተማ “ኪቲሜ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌላ ጣቢያ እያስገነባ ይገኛል።
በምስራቅ አዲስ አበባ ተፋሰስ ስር ያሉት የጎሮ እና የኪቲሜ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያዎች፤ ግንባታቸው ሲጠናቀቅ በየዕለቱ በድምሩ 106 ሺህ ሜትር ኪዩብ ወይም 106 ሚሊዮን ሊትር ፍሳሽ ቆሻሻ የማጣራት አቅም ይኖራቸዋል።
ከትላንት በስቲያ ግንባታው የተጀመረው የጎሮ ማጣሪያ ጣቢያ፤ የ205 ኪሎ ሜትር ቀላል እና ከባድ የፍሳሽ ቆሻሻ ማሰባሰቢያ መስመር ይዘረጋለታል ተብሏል።
🔴 ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17100/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram