avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
13.01.2026 22:15
ላለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ሲተገበር የነበረው የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) መርሃ-ግብር “ስህተት” እንደነበር የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ተናገሩ።

በሀገሪቱ የተለያዩ ከተሞች የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባለቤት እንዲሆኑ፤ ዜጎች የተመዘገቡበት መንገድ “ትክክል አልነበረም” ሲሉም ተችተዋል።

ወ/ሮ ጫልቱ ይህንን ያሉት፤ የሚመሩት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ያስገነባቸው ቤቶች ለምርቃት መብቃታቸውን በተመለከተ ዛሬ ማክሰኞ ጥር 5፤ 2018 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

በቤተሰብ ደረጃ 150 ሰዎችን እንዲይዙ ተደርገው የተገነቡት እነዚህ ቤቶች በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተመረቁት ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ነበር።

ባለፉት 17 ዓመታት በከተሞች ሲተገበር የነበረው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ፤ በከተሞች ያለውን የመኖሪያ ቤቶች ችግር “በተወሰነ ደረጃ ያቃለለ” መሆኑን በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ የጠቀሱት ወ/ሮ ጫልቱ፤ ሆኖም መርሃ-ግብሩ “ስህተት” እንደነበር ገልጸዋል።

መርሃ-ግብሩ “የመንግሥት ተሳትፎ የበዛበት” እና “ሁሉንም ዜጎች የቤት ባለቤት ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ” መሆኑ “ስህተት” እንደሆነም አስረድተዋል።

ሚኒስትሯ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች መርሃ ግብር ጋር በተያያዘ የነቀፉት ሌላው ነጥብ፤ የቤት ፈላጊ ዜጎች ምዝገባ የተከናወነበት መንገድ ነው።

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ሲገነቡ መጀመሪያ የታለመው ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች ቢሆንም፤ አብዛኞቹ በቤቶች ውስጥ የሚኖሩት ግን “ተከራዮች” መሆናቸው በሚኒስትሯ መግለጫ ላይ ተነስቷል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17082/

@EthiopiaInsiderNews
18
👎 17
👏 4
💩 1
16 7.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram