በአማራ ክልል ያሉ የጤና ባለሙያዎችን በውሰት በማዘዋወር ማሰራት “ላልተወሰነ ጊዜ” ታገደ
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ባለሙያዎችን በውሰት የማዘዋወር አሠራር ከነገ ጥር 1፤ 2018 ጀምሮ “ላልተወሰነ ጊዜ” መታገዱን አስታወቀ። የቢሮው አንድ የሥራ ኃላፊ፤ የውሰት ዝውውር ላልተወሰነ ጊዜ የታገደው “ከመመሪያ ውጭ የሆኑ” እና “ያልተገቡ አሠራሮች” በመስተዋላቸው መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ እገዳውን ያስተላለፈው፤ “የውሰት ዝውውርን በተመለከተ” ባለፈው ሰኞ ታኅሳስ 27፣ 2018 በጻፈው ደብዳቤ ነው።
በክልሉ ዞኖች እና የከተማ አስተዳደሮች ስር ላሉ ጤና መሪያዎች እና ሆስፒታሎች የተጻፈው ይኸው ደብዳቤ፤ የመንግሥት ሠራተኞች የምልመላና መረጣ መመሪያን መሰረት በማድረግ የጤና ባለሙያዎች ከአንድ ተቋም ወደ ሌላ ተቋም በውሰት በመዛወር ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሷል።
በደብዳቤው የተጠቀሰው መመሪያ፤ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች “አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ” አንድን ሠራተኛ ከመንግሥት ልማት ድርጅት፣ ከክልል መንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም መንግሥታዊ ካልሆነ ድርጅት “ከአንድ ዓመት ላልበለጠ ጊዜ” በውሰት አዘዋውረው እንዲያሰሩ ይፈቅዳል።
ሠራተኛው የውሰት ጊዜው ከተጠናቀቀ በኋላ ወደነበረበት መሥሪያ ቤት የመመለስ ግዴታ እንዳለበትም መመሪያው ይደነግጋል። ሆኖም በተጨባጭ የሚታየው አሠራር፤ ከአምስት ዓመት በፊት የአማራ ክልል የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አሻሽሎ ያወጣውን ይህ መመሪያ ያላከበረ ሆኖ ተገኝቷል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17074/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram