avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
06.01.2026 19:58
የአዲስ አበባ አቅመ ደካሞች ስለ በዓል እና ኑሮ ውድነት ምን ይላሉ?

በአዲስ አበባ ከተማ የበርካታ ሸቀጣ ሸቀጦች እና የበዓል ምግብ ግብዓት የሆኑ ምርቶች ዋጋ መጨመር፣ ብዙ ቤተሰቦች በዓሉን እንዲሁ ‘ቀለል አድርገው’ እንዲያሳልፉ አስገድዷቸዋል። እንዲህ ያለው የዋጋ መጨመር የበዓሉን መንፈሳዊ እሴት ባይቀንሰውም፣ የተለመደውን ባህል ቀመስ አከባበር መቀየሩን ግን መታዘብ ይቻላል።

በበዓል ወቅት በመንግሥታዊና በግል ተቋማት ከሚደረጉ የማዕድ ማጋራት የሚቋደሱ ዜጎች ጥቂት አይደሉም። በዚህ ዓመትም የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ በማዕድ ማጋራት ከ300 ሺህ በላይ አቅመ ደካማ ወገኖች ተጠቃሚ መሆናቸው በከተማ አስተዳደሩ ተገልጿል።

ሀና ኃይሉ እንዲህ ካለው ድጋፍ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል ናት። ከ13 ዓመት ገደማ በፊት ኑሮዋን በቋሚነት በአዲስ አበባ የመሰረተችው ሀና፤ "በዓልን ደስ ብሎኝ ውዬ አላውቅም" ትላለች።

ወደ አዲስ አበባ ከመጣች በኋላ በነበሩት ዓመታት፤ ጎመን ነግዳና በሰው ቤት የታዘዘችውን ሠርታ የእለት ጉርሷንም ሆነ በዓል ማሳለፊያ ገንዘብ አታጣም ነበር።

"ያኔ ኑሮም ደኅና ነበር። ያኔ ኑሮም ደኅና ነበር። አሁን ግን ሁሉም ተወደደ” ስትል ኑሮ እንደከበዳት ትናገራለች።

የጉሊት ነጋዴዋ ወ/ሮ ውዴ ቱሉ ይህንኑ ትጋራለች። ከመኖሪያዋ በቅርብ ርቀት የሚገኘው፤ ከየረር-በር ወደ ጎሮ በሚወስደው መንገድ የነበረው የጉሊት ስፍራ ፈርሶ ከመነሳቱ በፊት በዚያ ብዙ ደንበኛ ካላቸው ነጋዴዎች መካከል ነበረች።

🔴ሙሉውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17061/

@EthiopiaInsiderNews
10
😭 6
👎 2
2 9.5K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram