avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
05.01.2026 21:28
በመጪው ጠቅላላ ምርጫ ለውድድር የሚቀርቡ ዕጩዎች እና መራጮች በዲጂታል አማራጭ መመዝገብ የሚችሉበት መተግበሪያ እና የድረ ገጽ አማራጭ ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የዲጂታል አማራጮቹ፤ በስድስት የሀገሪቱ ቋንቋዎች ምዝገባ ለማከናወን እንዲችሉ ተደርገው መዘጋጀታቸውም ተገልጿል።

ምርጫ ቦርድ ይህን የገለጸው፤ ዛሬ ሰኞ ታህሳስ 27፤ 2018 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደ የዲጂታል ምዝገባ ስርዓት ይፋ ማድረጊያ ስነ-ሥርዓት ላይ ነው።

የዲጂታል ምዝገባ ሥርዓቱ የሚያገለግለው ለመመዝገብ ብቻ መሆኑን በስነ-ሥርዓቱ ላይ የገለጹት የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ፤ ድምጽ ለመስጠት ግን ሁሉም መራጭ እንደወትሮው የተመዘገበበት የምርጫ ጣቢያ መሄድ እንደሚጠበቅበት አስረድተዋል።

ምርጫ ቦርድ ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ ይፋ ባደረገው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት፤ የዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ የድምጽ መስጪያ ዕለት ሰኞ ግንቦት 24፤ 2018 ነው።

ይኸው የጊዜ ሰሌዳ፤ የዕጩዎች ምዝገባ ከፊታችን አርብ ጥር 1 እስከ የካቲት 1 ድረስ ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚከናወን አስቀምጧል።

በቴክኖሎጂ የሚደረገው የመራጮች ምዝገባ ከመጪው ጥር ወር አጋማሽ እስከ መጋቢት 7 ድረስ እንደሚደረግም በጊዜ ሰሌዳው ላይ ተዘርዝሯል።

ይህንን ምዘገባ ለማድረግ መራጮች “ምርጫዬ” የሚል ስያሜ የተሰጠውን መተግበሪያ በሞባይል ስልካቸው ወይም በሌሎች መተግበሪያ በሚቀበሉ የኤሌክትሮኒክስ አማራጮች አውርደው መጠቀም እንደሚችሉ ገልጿል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17050/

@EthiopiaInsiderNews
10
😁 6
👍 3
8 8.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram