avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
05.01.2026 20:10
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በአምስት ዓመት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ አዲስ ዋና ዳይሬክተር ሊሾምለት ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ ወ/ሮ ሐይማኖት ዘለቀን በዕጩነት አቀረቡ።

ላለፉት 23 ዓመታት በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እና የመንግስት ተቋማት የሰሩት የወ/ሮ ሐይማኖት ሹመት፤ ነገ ማክሰኞ ታህሳስ 28፤ 2018 በሚካሄደው የፓርላማ መደበኛ ስብሰባ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን፤ መገናኛ ብዙኃን ተግባራቸውን በሕግ መሰረት ማከናወናቸውን ለማረጋገጥ ክትትል እና ቁጥጥር የማድረግ ስልጣን በአዋጅ የተሰጠውን መስሪያ ቤት ነው።

ላለፈው አንድ ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ ተቋሙን የመምራት እና የማስተዳደር ኃላፊነት ተረክበው ሲሰሩ የቆዩት ዶ/ር ሳምሶን መኮንን ነበሩ።
 
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን እና አለምአቀፋዊነት ጽህፈት ቤትን በምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲመሩ የቆዩት ዶ/ር ሳምሶን፤ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተሾሙት ባለፈው ዓመት ጥር ወር መጀመሪያ ላይ ነበር።

በ2013 ዓ.ም. በአዋጅ የተመሰረተው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ሁለተኛ ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር ሳምሶን፤ እስካለፈው ሳምንት ድረስ በስራ ገበታቸው ላይ እንደነበሩ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ “በገዛ ፍቃዳቸው ስራቸውን መልቀቃቸውንም” እነዚሁ ምንጮች ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የአዲስ ዋና ዳይሬክተርን ሹመት በተመለከተ ለፓርላማ ደብዳቤ የጻፉት ባለፈው ሐሙስ ነበር።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17042/

@EthiopiaInsiderNews
5
😁 3
🤔 3
10 7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram