በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ ላይ የተከሰተው ምንድነው?
በመተሐራ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው ፈንታሌ ተራራ ላይ እሳት መታየቱን ተከትሎ፤ ከትላንትና ጀምሮ ይህንኑ የሚያሳይ ፎቶዎች በማህበራዊ ብዙሃን መገናኛዎች ያጋሩ ግለሰቦች ክስተቱ “የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ” እንደሆነ ሲገልጹ ተስተውለዋል።
ፈንታሌ ተራራ በአፋር ክልል፣ ገቢ ረሱ ዞን፣ አዋሽ ፈንቲዓሌ ወረዳ እና በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ፈንታሌ ወረዳ መካከል የሚገኝ ነው።
የፈንታሌ እና በአቅራቢያው የሚገኘው ዶፋን ተራሮች፤ በአካባቢው በተደጋጋሚ ለተከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦች መነሻ እንደነበሩ የዘርፉ ባለሙያዎች በወቅቱ መግለጻቸው ይታወሳል።
በአፋር ክልል ለመጨረሻ ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተው ባለፈው ህዳር ወር አጋማሽ እንደሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጦችን ከሚመዘግበው ከ“ቮልካኖ ዲስከቨሪ” ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ሆኖም በፈንታሌ ተራራ ላይ ከአርብ ታህሳስ 24፤ 2018 ጀምሮ ቃጠሎ መከሰቱን ተከትሎ፤ ከስተቱን ከእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ጋር ያያዙት አሉ።
ይሁን እንጂ ክስተቱ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ውጤት ሳይሆን በሰዎች አማካኝነት የተቀሰቀሰ እና የተስፋፋ ሰደድ እሳት መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
በአፋር ክልል፣ የአዋሽ ፈንቲዓሌ ወረዳ ዛሬ እሁድ ከሰዓት ባሰራጨው መረጃም፤ በፈንታሌ ተራራ ላይ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ በእሳተ ገሞራ ፍንዳታ (ቮልካኖ) የተከሰተ እንዳልሆነ አረጋግጧል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አደን በላእ፤ የእሳት ቃጠሎው የተነሳው በመተሐራ ከተማ አቅራቢያ በኩል ባለው የተራራው ክፍል መሆኑን ተናግረዋል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17038/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram