የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተያዘው በጀት ዓመት ለሶስተኛ ጊዜ ለሚያከናውነው የመሬት ሊዝ ጨረታ፤ የሰነድ ሽያጩን ከመጪው ሰኞ ታህሳስ 27፤ 2018 ጀምሮ ለተከታታይ አስር ቀናት እንደሚያካሄድ አስታወቀ።
አስተዳደሩ ለዚህ ዙር ለጨረታ ያቀረባቸው ቦታዎች ብዛት 220 ነው።
ለንግድ ወይም ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉት እነዚህ ቦታዎች የሚገኙት፤ በየካ፣ በጉለሌ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በለሚ ኩራ፣ በቂርቆስ፣ በአዲስ ከተማ፣ በልደታ እና በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተሞች እንደሆነ ተገልጿል።
በአሁኑ ጨረታ የአራዳ እና የቦሌ ክፍለ ከተሞች አልተካተቱም።
ለአሁኑ ጨረታ የቀረቡት በዘጠኝ ክፍለ ከተሞች የሚገኙት ቦታዎች፤ አጠቃላይ ስፋታቸው 7.7 ሄክታር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።
ቦታዎቹ “ከፕላን ተቃርኖ እና ከይገባኛል የጸዱ መሆናቸውንም” ቢሮው አመልክቷል።
ባለፈው ጥቅምት ወር በተደረገው ተመሳሳይ የመሬት ሊዝ ጨረታ፤ ከአርሶ አደር መብት፣ ከፍርድ ቤት እግዶችና ከሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዙ ምክንያቶች 110 የሚሆኑት መሬቶች ከሂደቱ ውጭ መደረጋቸው የሚታወስ ነው።
በእዚህ ዙር ለሊዝ ጨረታ ቀርበው የነበሩ ቦታዎች ብዛት 384 ነበር።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17028/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram