avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
02.01.2026 22:16
“ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት” የተባለው የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ፤ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቅንጅት ምዝገባ ምስክር ወረቀት አገኘ።

የቅንጅቱ አካላት የሆኑ አራት ፓርቲዎች፤ በመጪው ምርጫው የሚወዳደሩ 1,200 ገደማ ዕጩዎችን አስቀድመው ማዘጋጀታቸውን ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

“ለኢትዮጵያ” በሚለው አጭር ቃል የሚጠራው ይኸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅንጅት፤ መመስረቱ ይፋ የተደረገው ባለፈው መስከረም ወር ነበር።

ቅንጅቱን የመሰረቱት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)፣ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አኢዴፓ)፣ እናት ፓርቲና እና አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ የተባሉ አምስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ናቸው።

ለእዚህ የፓርቲዎች ቅንጅት ምርጫ ቦርድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያዘጋጀው ህዳር 5፤ 2018 ቢሆንም፤ ለፓርቲዎቹ የደረሰው ግን ባለፈው ሰኞ ታህሳስ 20 መሆኑን ኢሕአፓ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጿል።

ከምዝገባ የምስክር ወረቀቱ ጋር ተያይዞ ለፓርቲዎቹ የተላከው የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ፤ በቅንጅቱ መንቀሳቀስ የሚችሉ አራት ፓርቲዎች ብቻ መሆናቸውን ይገልጻል።

ቦርዱ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር “ቅንጅት ለመመስረት የሚያስችለውን በአዋጅ የተቀመጠ መስፈርት አላሟላም” ያለውን እናት ፓርቲን ለጊዜው ከትብብሩ ውጭ አድርጎታል።

እናት ፓርቲ ቅንጅቱን ለመመስረት የወሰነበትን ጉባኤ ያደረገው “ባልተሟላ የላዕላይ ምክር ቤት አባላት” መሆኑን እና “ከአባላት የቀረበ ተቃውሞም” መኖሩን በመግለጽ ነው ምርጫ ቦርድ የፓርቲውን ጥያቄ ያልተቀበለው።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17023/

@EthiopiaInsiderNews
4
👍 3
👎 2
8 8.2K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram