avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
02.01.2026 20:39
የጋምቤላ ክልል ፖሊስን በኮሚሽነርነት የሚመሩት አቶ ኡጉላ ኡጁሉ ትላንት አመሻሹን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ አርያት ኡባንግ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።

የፌደራል ፖሊስ አባላት በጋምቤላ ከተማ ያሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ትላንት ሐሙስ በተንቀሳቀሱበት ወቅት፤ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በጋምቤላ ከተማ ባለ አንድ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ የከተማይቱ ነዋሪ፤ ትላንት ከእኩለ ቀን በኋላ በፌደራል ፖሊስ ተሽከርካሪዎች ሰዎች ታስረው ሲወሰዱ መመልከታቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እማኝነታቸውን ሰጥተዋል።

ከታሰሩት ሰዎች ውስጥ በክልሉ ባሉ የመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ እና የጸጥታ ኃይሎች እንደሚገኙበት አስረድተዋል።

ተጠርጣሪዎችን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል እንቅስቃሴ በሚደረግበት ወቅት፤ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር እኚሁ ነዋሪ ተናግረዋል።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው ሌላ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪም ይህንኑ አረጋግጠዋል። የተኩስ ድምጹ በዛሬው ዕለት እንደቆመ ሁለቱም ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በትላንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ከዋሉ ተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት የጋምቤላ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር፤ በፌደራል ፖሊስ አባላት ተይዘው ወደ ቤታቸው ለፍተሻ ከመወሰዳቸው አስቀድሞ በጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነበሩ ተብሏል።

🔴ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17017/

@EthiopiaInsiderNews
4
7 7.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram