avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
02.01.2026 13:13
ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሀዋሳ እና ደብረ ብርሀን ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ ዘጠኝ የማምረቻ ሼዶችን ለሶስተኛ ወገን ለማስተላለፍ ጨረታ አወጣ።

ኮርፖሬሽኑ ፋብሪካ ሼዶቹን በውስጣቸው ካሉ ማሽኖች እና ንብረቶች ጋር ጨረታ ያወጣባቸው፤ ማምረቻዎቹ “በተለያዩ ምክንያቶች ምርት በማቆማቸው” እንደሆነ ገልጿል።

ከመንግስት ግዙፍ የልማት ድርጅቶች አንዱ የሆነው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፤ በሀዋሳ እና ደብረ ብርሀን የሚገኙትን ጨምሮ 10 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና ሁለት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በስሩ የሚያስተዳድር ነው።

የካፒታል መጠናቸው ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሆነ፣ ከ50 ሄክታር በላይ የቆዳ ስፋት ያላቸውን እና ሌሎች መስፈርቶችን ያሟሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን፤ ኮርፖሬሽኑ ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንነነት ያሳደገው በህዳር 2017 ዓ.ም ነው።

ይህንን ደረጃ ካገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል አንዱ በሆነው የሀዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ውስጥ ካሉ አምራቾች መካከል በስምንቱ ላይ ኮርፖሬሽኑ ጨረታ አውጥቶባቸዋል።

ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን ያወጣው፤ ከተቋሙ ጋር ውል የገቡ አምራቾች በውላቸው መሰረት ማምረት ባለመቻላቸው ምክንያት እንደሆነ የኮርፖሬሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ጳውሎስ በለጠ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

አምራቾቹ ወደ ስራ እንዲገቡ በተደጋጋሚ ጥረት መደረጉን የገለጹት አቶ ጳውሎስ፤ ይህ ባለመሳካቱ ማምረቻ ቦታዎቹ (ሼዶች)፣ ማሽኖች እና መሰል ንብረቶች ለሶስተኛ ወገን በጨረታ ለማስተላለፍ ተቋሙ መወሰኑን ገልጸዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17008/

@EthiopiaInsiderNews
5
👏 3
😁 3
11 6.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram