avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
01.01.2026 20:37
“የቤት ባለቤት እናደርጋችኋለን” በሚል ባለፈው ዓመት ከሕዝብ ወደ 1.5 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ “ያጭበረበሩ” ሰዎች መከሰሳቸውን ፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ።

እንደዚህ አይነት “ማጭበርበር” በሚፈጽሙ ድርጅቶችና ግለሰቦች ምክንያት፤ ዜጎች “ገንዘብ ይዘው እንኳን ያለ ስጋት ቤት ለመግዛት እየተቸገሩ” መሆኑን አንዲት የፓርላማ አባል ተናግረዋል።

አፀደ ማሞ የተባሉት እኚሁ የፓርላማ አባል፤ በሀገር ደረጃ “ከፍተኛ ትኩረት” ተሰጥቷቸው እየተሰሩ ካሉ ጉዳዮች ውስጥ “የዜጎች የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ማድረግ” አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል።

ገዢው ብልጽግና ፓርቲን ወክለው ከአማራ ክልል ዳባት ምርጫ ክልል የተመረጡት የፓርላማ አባሏ፤ “ ‘ቤት ሰርተን እንስረክባለን’ በማለት የህዝብን ገንዘብ ሰብስበው ከሀገር የሚወጡ” ድርጅቶች እንዳሉ ገልጸዋል።

በቤት ልማት ዘርፍ ከተሰማሩ የግል ድርጅቶች ውስጥ “በውላቸው መሰረት በጊዜ ሰርተው የማያስረክቡ”፣ “ሰነድ የሚያጨበርብሩ” እና “በጣም ውስብስብ የሆነ ሰነድ በማስፈረም በየጊዜው ያለ ምክንያት ገንዘብ የሚጨምሩ” እንዳሉ ወ/ሮ አፀደ አስረድተዋል።

እንደዚህ አይነት ጉዳዮች ሲቀርቡ፤ “የህዝብን ጥቅም ከማስጠበቅ” እና “ፍትህ ከማስፈን” አንጻር ፍትሕ ሚኒስቴር ምን እየሰራ እንደሆነም የፓርላማ አባሏ ጠይቀዋል።

የፓርላማ አባላትን ጥያቄ ለመመለስ ዛሬ ሐሙስ ታኅሣሥ 23 በተካሔደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ የተገኙት የፍትህ ሚኒስትሯ ሃና አርዓያሥላሴ፤ ከህዝብ ንብረት ሰብስበው ከዳር ሳያደርሱ “የሚሰወሩ እና የሚጠፉ አካላትን በተመለከተ የወንጀል ተጠያቂነትን እያሰፈንን እንገኛለን” ብለዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

🔴በቪዲዮ ለመመልከት➡️ https://youtu.be/wjhiNMh3wI8

@EthiopiaInsiderNews
10
👍 4
10 7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram