avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
01.01.2026 19:37
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ ከ40 በላይ መንግስታዊ የልማት ድርጅቶችን የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፤ አዲስ የሙስና ጥቆማ መቀበያ ስርዓት ማዘጋጀቱን ይፋ አደረገ።

ይህ ስርዓት ማንኛውም ግለሰብ ባለበት ሆኖ ሚስጥራዊነቱ በተጠበቀ መልኩ ጥቆማ ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።

አደራ” የሚል ስያሜ ያለው የሙስና ጥቆማ መስጪያ ስርዓት በአሁኑ ወቅት በድረ ገጽ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በቅርቡ ወይም በሞባይል መተግበሪያ (አፕልኬሽን) መልኩ ለተገልጋዮች ይቀርባል ተብሏል።

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ሰራተኞች እንደለማ የተነገረለት ይህን ድረ ገጽ ተጠቅሞ፤ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች ጥቆማዎችን ማቅረብ እንደሚቻል መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።

በቀጣይ ግን በአፋን ኦሮሞ እና በትግርኛ ቋንቋዎች የሙስና ጥቆማዎችን መስጠት እንደሚቻል መስሪያ ቤቱ ዛሬ ሐሙስ ታኅሣሥ 23፤ 2018 በሰጠው መግለጫ ላይ ተጠቅሷል።

መግለጫውን የሰጡት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሀብታሙ ኃይለሚካኤል፤ ይህንን የጥቆማ መስጫ ስርዓት መዘርጋት ያስፈለገው፤ በመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ ሙስና እንዳይፈጸም እና ከተፈጸመ ደግሞ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በማሰብ እንደሆነ ተናግረዋል።

🔴ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/16991/

🔴 መግለጫውን በቪዲዮ ለመመልከት ➡️ https://youtu.be/Il_7U_oeWx4

@EthiopiaInsiderNews
14
😁 9
👏 3
11 6.2K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram