ቪዲዮ:- በአማራ ክልል ካለው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው ግለሰቦች የፍርድ ሂደት መጓተት በፓርላማ ጥያቄ አስነሳ። ጥያቄው የተነሳው ዛሬ ሐሙስ ታኅሣሥ 23፤ 2018 በተካሔደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተመራጩ ዶ/ር አበባው ደሳለው “ከ2 ዓመት ከ6 ወር በላይ” ታስረው የሚገኙ የአማራ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች ላይ ላቀረበው ክስ የፍትህ ሚኒስቴር ማስረጃ “ማቅረብ ባለመቻሉ ፍትህ አጥተው” እንደሚገኙ አመልክተዋል። ሚኒስቴሩ ማስረጃና ምስክር ማቅረብ ካልቻለ ክሱን “እንዲያቋርጥም” ጠይቀዋል።
በዛሬው የፓርላማ ስብሰባ ተገኝተው ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የፍትህ ሚኒስትሯ ሃና አርዓያሥላሴ ፤ “እኛ ምስክር ሳናቀርብ የተጓተተ እና የተቋረጠ ክስ የለም” ብለዋል። የፍትህ ሂደቱ የተጓተተው ከክሱ አይነት ጋር በተገናኘ ምክንያት እንደሆነ ሚኒስትሯ ተናግረዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
🔴 ዝርዝሩን በጹሁፍ ለማንበብ 👉
https://ethiopiainsider.com/2026/17005/
🔴 ለሚኒስትሯ የቀረበውን ጥያቄ እና ምላሻቸውን ይህን ሊንክ ተጭነው ይመልከቱ 👉
https://youtu.be/yMz-TyhP3Ok?si=SNbIKY2i22EzHpLw
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram