በግጭት ውስጥ የሰነበተው የጋምቤላ ክልል ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ምን ይመስላል?
በጋምቤላ ክልል አንጻራዊ መረጋጋት መስፈኑን እና ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው “እየተመለሱ መሆናቸውን” የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ። የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው አካባቢያቸው ቀስ በቀስ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እየተመለሰ ቢሆንም ትምህርት ቤቶች አሁንም ዝግ መሆናቸውን እና አልፎ አልፎ ምሽት ላይ የተኩስ ድምጾች እንደሚሰሙ ተናግረዋል።
የክልሉ ዋና መቀመጫ በሆነችው ጋምቤላ ከተማ ህዳር 28፤ 2018 በተፈጸመ ጥቃት አንድ ሰው መገደሉን እና ሌላ ግለሰብ መቁሰሉን ተከትሎ፤ በጋምቤላ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በግጭቶች ውስጥ ቆይተዋል።
ግጭቱ ይበልጥ የተባባሰው፤ የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ዋና ኢንስፔክተር ኡሞድ ኡጁሉ ከሁለት ሳምንት በፊት ማክሰኞ ታህሳስ 7 ከተገደሉ በኋላ ነበር።
የጋምቤላ ክልልን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ፤ አሁን በክልሉ ያለው ሁኔታ “ተረጋግቷል” ብለዋል። በክልሉ በሰፈነው አንጻራዊ ሰላም ምክንያት ነዋሪዎች ወደ ስራ ገበታቸው “እየተመለሱ” መሆናቸውንም ወ/ሮ አለሚቱ አክለዋል።
እንደ ሌሎቹ የክልሉ አካባቢዎቹ ሁሉ የጋምቤላ ከተማ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች መሆኗን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሯ፤ ለዚህም በከተማይቱ የሚገኙ የንግድ ሱቆች እና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት “በሙሉ” ወደ ስራ በመግባት ላይ መሆናቸውን በማሳያነት ጠቅሰዋል።
“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎችም ይህንኑ አረጋግጠዋል።
🔴ለዝርዝሩ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16981/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram