avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
29.12.2025 23:07
የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን በትግራይ ክልል የሚያከናወነውን የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት እና የመበተን (demobilization) ሥራ ከመስከረም ወር ጀምሮ “ላልተወሰነ ጊዜ” እንደተቋረጠ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጸ።

በዚህ ምክንያት በክልሉ የሚገኙ የቀድሞ ተዋጊዎችን መረጃ በዲጂታል መንገድ የሚመዘግቡ 67 ባለሙያዎችን የኮንትራት የሥራ ውል ከአንድ ሳምንት በኋላ እንደሚያቋርጥም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ተስፋአለም ይሕደጎ፤ ከትግራይ ክልል በመጀመሪያው ዙር ትጥቅ ፈትተው እና ስልጠና ወስደው ወደ ህብረተሰቡ የተቀላቀሉ የቀድሞ ታጣቂዎች ብዛት ከ63,300 በላይ እንደሆነ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

እነዚህ የቀድሞ ታጣቂዎች ስልጠና የወሰዱት፤ በመቐለ፣ እዳጋ ሀሙስ እና አድዋ ከተሞች በሚገኙ ማዕከላት እንደሆነም ገልጸዋል።

በመጀመሪያ ዙር የቀድሞ ታጣቂዎችን “ዲሞቢላይዝ” ለማድረግ ከተያዘው እቅድ አንጻር፤ በክልሉ 11 ሺህ ገደማ የሚሆኑ ታጣቂዎች ላይ የትጥቅ ማስፈታቱ እና የመበተኑ ስራ እስካሁንም አለመከናወኑን ምክትል ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።

ይህ ሥራ ማለቅ የነበረበት እስካለፈው መስከረም ወር ድረስ እንደነበርም አቶ ተስፋአለም አክለዋል። “የፖለቲካ ትኩሳት በዚህም በዛም” መኖሩ ሂደቱን ማስቀጠል እንዳይቻል “ፈታኝ ሁኔታ” መፍጠሩን ምክትል ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

“ዲሞቢላይዝ” ለማድረግ አመራሮቹም፣ ታጣቂዎቹም “ፈቃደኛ ሆነው መምጣት ይጠበቅባቸዋል” ሲሉ ሂደቱ ለምን እንደተቋረጠ አብራርተዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15287/

@EthiopiaInsiderNews
7
👎 1
😁 1
11 7.2K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram