ሶማሌላንድን “የግዛቴ አካል ነች” የምትለው ሶማሊያ፤ ይህን አቋሟን ወደ ጎን በማድረግ እስራኤል የሰጠችውን የነጻ ሉዓላዊ ሀገርነት እውቅና በተመለከተ እስካሁን በይፋ ያለችው ነገር የለም። ትላንት ምርጫ ስታካሂድ የዋለችው ሶማሊያ ይፋዊ መግለጫ ባትሰጥም፤ በጉዳዩ ላይ ለመወያየት የሀገሪቱ መንግስት ካቢኔ ዛሬ ምሽቱን አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚቀመጥ ተዘግቧል።
ከሶማሌላንድ ጋራ በፈጸመችው የመግባቢያ ስምምነት ምክንያት ከሶማሊያ ጋራ የተካረረ ውጥረት ውስጥ ገብታ የነበረችው እና በርካታ ተቃውሞዎችን ያስተናገደችው ኢትዮጵያም፤ በእስራኤል እርምጃ ዙሪያ እስካሁን በይፋ መግለጫ አልሰጠችም። ኢትዮጵያ እስካሁን በይፋ ምንም ባትልም፤ የቀድሞው የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ብርሃኑ ሌንጂሶ ለሶማሌላንድ “የእንኳን ደስ አላችሁ” መልዕክት አስተላልፈዋል።
የኢትዮጵያ ባላንጣ ተደርጋ የምትወሰደው ግብጽ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቷ በኩል ዛሬ ምሽት ባወጣችው መግለጫ፤ እስራኤል ለሶማሌላንድ የሰጠችውን የሀገርነት እውቅና ተቃውማለች። ግብጽ መግለጫውን ያወጣችው፤ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ባድር አብደልላቲ በጉዳዩ ላይ ከጅቡቲ እና ቱርክ አቻዎቻቸው ጋር በጉዳዩ ዙሪያ በስልክ መወያየታቸውን ተከትሎ ነው።
ሶስቱ ሀገራት የእስራኤል ድርጊት የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የሚጥስ ነው” ማለታቸውን የጠቀሰው የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ በጉዳዩ ላይ ከሞቃዲሾ ጎን እንደሚቆሙ ማሳወቃቸውንም አክሏል። እነዚሁ ሀገራት ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋራ የተፈራረመችውን የመግባቢያ ስምምነት፤ በ“ጽኑ በማውገዝ” ለሶማሊያ አጋርነታቸውን ከገለጹ ሀገራት መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው።
🔴 ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16930/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram