avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
26.12.2025 14:34
ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ የፕላስቲክ ምርቶችን (ፌስታል) ከአንድ ወር በኋላ መጠቀም የሚከለክለው አዋጅ የትግበራ ጊዜ እንዲራዘምላቸው ሱፐርማርኬቶች እና አምራቾች ጠየቁ።

የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በበኩሉ አዋጁ ተግባራዊ ከመደረጉ አስቀድሞ የተሰጠው የስድስት ወራት የሽግግር ጊዜ እንደማይራዘም ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታውቋል።

በግንቦት 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ የጸደቀው ይህ አዋጅ፤ “የደረቅ ቆሻሻ አያያዝ እና አወጋገድን” የሚመለከት ሲሆን ለ13 ዓመታት በስራ ላይ የቆየውን ነባር ህግ የተካ ነው።

አዲሱ አዋጅ “ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል ፕላስቲክ ማምረት፣ ለገበያ ማቅረብ፣ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት፣ መሸጥ፣ ማከማቸት ወይም መጠቀምን” ከልክሏል።

ክልከላውን ተላልፈው በተገኙ አምራቾች እና ተገልጋዮች ላይ የህግ ተጠያቂነት የሚያስከትለው የእዚህ አዋጅ አፈጻጸም፤ በረቂቅ ደረጃ ለፓርላማ ከቀረበ ጊዜ አንስቶ ሲያነጋግር ቆይቷል።

ስስ ፌስታሎችን በብዛት የሚጠቀሙ የንግድ መደብሮች፤ ለአንድ ጊዜ አገልግሎት የሚውሉ የፕላስቲክ ከረጢቶችን የሚተኩ “አማራጭ ምርቶች” “በገበያ ላይ እንደልብ አለመኖራቸው” አዋጁን በተቀመጠለት ጊዜ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅፋት እንደሚሆን ያስረዳሉ።

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር ያለው የኩዊንስ ሱፐር ማርኬት ዋና ስራ አስኪያጅ ሰሚራ ሸረፋ፤ አዋጁ መውጣቱን ተከትሎ ስስ ፌስታሎችን ላለመጠቀም የሚችሉትን ቢያደርጉም፤ እስካሁን “ምትክ ምርት” ማግኘት አለመቻላቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ስራ አስኪያጇ ያለ ስስ ፌስታል አገልግሎት መስጠት ፈታኝ ነው ባይ ናቸው።

🔴ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16922/

@EthiopiaInsiderNews
10
👎 1
11 7.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram