መረጃ በሚከለክሉ ኃላፊዎች ላይ በመረጃ ነጻነት ረቂቅ አዋጅ የተቀመጠው የቅጣት መጠን፤ ከ20 ሺህ ወደ 150 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ከፍ እንዲል የኢትዮጵያ ብዙሃን መገናኛ ምክር ቤት ጠየቀ።
መረጃዎችን በሰነድ መስጠት ሳይቻል ሲቀር፤ ኃላፊዎች በቃለ መጠይቅ ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲሰጡ የሚያስገድድ አንቀጽ በአዋጁ ላይ መስፈር እንዳለበትም ምክር ቤቱ አሳስቧል።
ምክር ቤቱ ይህን ጥያቄ ያቀረበው፤ የመረጃ ነጻነት የአዋጅ ረቂቅን በተመለከተ ዛሬ ሐሙስ ታኅሣሥ 16፤ 2018 በአዲስ አበባ በተካሄደ ውይይት ላይ ነው።
በፍትሕ ሚኒስቴር ስር ተዋቅሮ በነበረው የመገናኛ ብዙሃን የስራ ቡድን የተዘጋጀው እና በኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የዳበረው የመረጃ ነጻነት የአዋጅ ረቂቅ፤ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይላካል ተብሎ ይጠበቃል።
ምክር ቤቱ አዋጁን ከማጽደቁ በፊት፤ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተጠርተው የሕዝብ አስተያየት እንዲካተትበት እንደሚደረግም በዚህ ውይይት ላይ ተነስቷል።
በዚሁ እሳቤ በተዘጋጀው በዛሬው የውይይት መድረክ ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት በአዋጅ ረቂቁ ላይ መሻሻል ይገባቸዋል ባላቸው ጉዳዮች ላይ ምክረ ሃሳቦችን አቅርቧል።
ተቋማት ወይም የተቋማት ኃላፊዎች መረጃ ሲጠየቁ “በ48 ሰዓት ውስጥ ምላሽ መስጠት አለባቸው” በሚል በአዋጁ ረቂቁ ላይ የተቀመጠው አንቀጽ በምክር ቤቱ እንዲሻሻል ከተጠየቁት ውስጥ ይገኝበታል።
የመረጃ መስጪያ ገደቡ ለአስቸኳይ ጉዳዮች ሲሆን “ከዚያም ባጠረ ጊዜ እንዲሰጥ” የሚል ሀሳብ “ሊካተት ይገባል” ሲል ምክር ቤቱ የማሻሻያ ሃሳቡን ገልጿል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16910/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram