“ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ” የተሰኘ ድርጅት፤ ዓለም-አቀፋዊ እና ሕገ-መንግስታዊ “ግዴታቸውን እና ኃላፊነታቸውን ባለመወጣት” “በተፈናቃዮች ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲደርሱ አድርገዋል” ያላቸውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ የሰላም ሚኒስቴር እና ሶስት ክልሎችን በፍርድ ቤት ከሰሰ። ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ለመመልከት ለነገ አርብ ለታኀሣሥ 17፤ 2018 ቀጠሮ ሰጥቷል።
ሀገር በቀል የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ የክስ ማመልከቻውን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ችሎት ያስገባው ባለፈው ጥቅምት 25፤ 2018 ነው።
በዳኞች በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት የክስ መዝገቡ እንዲከፈት የተደረገው ህዳር 5 ቢሆንም፤ ችሎቱ የክስ መዝገቡን ለመመልከት ቀጠሮ የሰጠው ለታኀሣሥ 10 ነበር።
ሆኖም በዕለቱ ዳኞቹ ባለመሟላታቸው ምክንያት ችሎቱ መዝገቡን ለመመልከት የሰጠውን ቀጠሮ በአንድ ሳምንት አራዝሟል።
ድርጅቱ ክሱን ያቀረበው በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች ውስጥ ለተፈናቀሉ “የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ዜጎች ጥቅም” መሆኑን በክስ ማመልከቻው ላይ ገልጿል።
የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ከአፋር፣ ትግራይ፣ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ላይ “ደርሷል” ያለውን “የሰብአዊ መብት ጥሰት” በክስ ማመልከቻው በዝርዝር አስፍሯል።
ድርጅቱ በክሱ በመጀመሪያ ላይ የጠቀሰው፤ ህዳር 24፤ 2013 በትግራይ ክልል የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ ከትግራይ ምዕራባዊ ዞን እና ከአፋር ክልል ሸኸት ወረዳ የተፈናቀሉ ሰዎችን ጉዳይ ነው። በዚሁ ጦርነት “ከአንድ ሚሊዮን 57 ሺህ በላይ” የትግራይ ተወላጆች መፈናቀላቸውን ድርጅቱ አመልክቷል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16902/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram