ቪዲዮ፦ የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት “በቀይ ባህር አፋር ህዝቦች” ላይ በኤርትራ መንግሥት እየተፈፀመ ያለውን “የሰብዓዊ መብት ጥሰት” በተመለከተ ለአፍሪካ የሰብዓዊ እና ህዝቦች መብቶች ኮሚሽን ያቀረበው ክስ “ተቀባይነት ማግኘቱን” ገለጸ። ድርጅቱ ይህን ያሳወቀው ዛሬ ታሕሣሥ 15፤ 2018 በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል በሰጠው መግለጫ ነው።
የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ኢብራሂም ሀሩን፤ በኤርትራ መንግሥት ላይ ያቀረቡት የክስ አቤቱታ 122 ገፅ መሆኑን ተናግረዋል። ክሱን የተቀበለው የአፍሪካ የሰብዓዊ እና ህዝቦች መብቶች ኮሚሽን፤ የኤርትራ መንግሥት በ60 ቀናት ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥበት ክሱን ታኅሣሥ 2፤2018 መላኩን “አሳውቆናል” ብለዋል።
የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት “የራስን ዕድል በራስ መወሰን እስከመገንጠል” የሚል ዓላማ አንግቦ፤ ለ28 ዓመታት ያህል የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ የሚገኝ ነው። ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መንግሥት ስለሚደረግለት “ድጋፍ” ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ኢብራሂም ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት “የትጥቅም ይሁን ሌሎች ድጋፎችን እንደማያደርግላቸው” አስተባብለዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
🔴 በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ለተነሱ ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾችን በቪዲዮ ለመመልከት ይህን ሊንክ ይጫኑ ➡️
https://youtu.be/WedzG3qiiw8
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram