avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
24.12.2025 16:05
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምሥረታ ላይ ያሉ “የኮንቶማ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” እና “የደንጣ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዳያካሂዱ በጸጥታ ኃይሎች መከልከላቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

በዜጎች የመደራጀት እና የፖለቲካ ፓርቲ የመመሥረት ዴሞክራሲያዊ መብት ላይ “የማስተጓጎል ተግባራት” የሚፈጽሙ አካላት ላይ የክልሉ የመንግሥት “ተገቢውን የእርምት እርምጃ” እንዲወስዱ ቦርዱ “በጥብቅ” አሳስቧል።

ምርጫ ቦርድ ዛሬ ረቡዕ ታህሳስ 15፤ 2018 ባወጣው መግለጫ፤ የሁለቱም ፓርቲዎች ተወካዮች ፓርቲ ለመመሥረት የሚያስፈልጉ ሁሉንም ሕጋዊ ሠነዶች አሟልተው ጠቅላላ ጉባዔያቸውን እንደሚያካሄዱ ለቦርዱ አሳውቀው እንደነበር ጠቅሷል።

በዚህም መሰረት የኮንቶማ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጥቅምት 30 በቡታጅራ ከተማ፤ የደንጣ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ደግሞ ታኅሣሥ 12 በሀድያ ዞን ቢጠና ታዳጊ ከተማ የምሥረታ ጠቅላላ ጉባዔያቸውን ለማድረግ ሲሞክሩ ክልከላ እንደገጠማቸው ገልጿል።

የኮንቶማ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲን ጉባዔ፤ ቦርዱ የወከላቸው ባለሙያዎች በሕጉ መሠረት በቦታው በአካል በመገኘት ታዝበው ሪፖርት እንዲያቀርቡ ተመድበው እንደነበር ምርጫ ቦርድ በዛሬው መግለጫው አመልክቷል።

ጉባኤው ከመደረጉ አስቀድሞም፤ የፓርቲው መሥራቾች ትብብር እንዲደረግላቸው ለክልሉ መንግሥት አስተዳደር እና በየደረጃው ላሉ የመንግስት እና የጸጥታ አካላት በደብዳቤ ማሳወቁን ቦርዱ አስረድቷል።

ሆኖም በጉባኤው ዕለት “መሣሪያ የታጠቁ” የቡታጅራ ከተማ የጸጥታ አካላት፤ “ከተማው በኮማንድ ፖስት ሥር ስለሆነች መሰብሰብ አይቻልም” በሚል መከልከላቸውን ቦርዱ አስታውቋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16887/

@EthiopiaInsiderNews
🤬 7
6
7 6.4K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram