በኢትዮጵያ “የሀሳብ ትግል” ለሚያደርጉ ሁሉ በነጻነት የሚንቀሳቀሱበት “ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል” ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ።
ከወረዳ እስከ ፌዴራል ያሉ ተቋማትን እንዲመሩ የተሾሙ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት፤ በሚያከናውኗቸው ስራዎች እና ውሳኔዎቻቸው ላይ “ማንም ጣልቃ እንዳይገባባቸው አድርገናል” ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ካሉት ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶች አንዱ የሆኑት አቶ አደም ይህን ያሉት፤ ለገዢው ፓርቲው ቅርበት ካለው ፋና የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ነው።
ትላንት ሰኞ ታህሳስ 13፤ 2018 በተላለፈው በዚሁ ቃለ ምልልስ ላይ ከተነሱ ጉዳዮች ውስጥ “ሀሳብ አልባ ፖለቲካ” እና የመጪው ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ ይገኙበታል።
በኢትዮጵያ “በሀሳብ ልዕልና ላይ የተመሰረተ ስርዓት” የበላይነት እንዲይዝ “የፖለቲካ ምህዳሩን ማስፋት” እና “ጤናማ ማድረግ” አስፈላጊ መሆኑን በቃለ ምልልሳቸው ላይ የጠቀሱት አቶ አደም፤ ከዚህ አኳያ ባለፉት ዓመታት በተሰራው “ሪፎርም” ስኬት መመዝገቡን ተናግረዋል።
በሀገሪቱ ውስጥ “አማራጭ ሃሳብ አለኝ” የሚል አካል፤ “በሙሉ በነጻነት መንቀሳቀስ እንዲችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮለታል” ሲሉም ተደምጠዋል። “በአሁኑ ወቅት ‘ሃሳብ አለኝ፣ የራሴን ፓርቲ መስርቼ መታገል እፈልጋለሁ’ የሚል አካል ላይ እንቅፋት የሚፈጥር አካል የለም” ሲሉም አክለዋል።
እርሳቸው ይህን ቢሉም፤ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅና አግኝተው የፖለቲካ እንቅስቃሴ እያደረጉ ያሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጉባኤዎቻቸውን ጨምሮ መደበኛ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ እንዳልቻሉ ወቀሳ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
🔴 ለዝርዝሩ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16867/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram