የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR)፤ በጋምቤላ ክልል የተጠለሉ ስደተኞች ላይ በማነጣጠር በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ “የተሳሳቱ መረጃዎች” “በእጅጉ እንዳሳሰቡት” ገለጸ።
ለሁኔታው በአፋጣኝ መፍትሔ ካልተበጀለት በአካባቢው ውጥረትን ሊያባብስ እንደሚችል ድርጅቱ አስጠንቅቋል።
የተመድ የስደተኞች መርጃ ተቋሙ ማስጠንቀቂያውን የሰጠው፤ ዛሬ ማክሰኞ ታህሳስ 14፤ 2018 ባወጣው መግለጫ ነው።
ድርጅቱ በዚሁ መግለጫው፤ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በሀገራቸው ከሚደርስባቸው ጥቃት “ደህንነትን እና ጥበቃን ለማግኘት” እንደሆነ አስታውሷል።
የጥገኝነት ሲቪል እና ሰብአዊ ባህሪያት “ለድርድር የማይቀርብ መርህ” መሆኑን በመግለጫው አጽንኦት የሰጠው ድርጅቱ፤ “በትጥቅ እንቅስቃሴ” ውስጥ ሲሳተፍ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ በሀገሩ ሕግ መሰረት ተጠያቂ እንደሚሆን አመልክቷል።
ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጩ መረጃዎች፤ ከደቡብ ሱዳን ተፈናቅለው በጋምቤላ ክልል ተጠልለው የሚገኙ ስደተኞች በክልሉ ሰሞኑን በተቀሰቀሰው ግጭት ውስጥ ተሳትፎ እንዳላቸው ወንጅለው ነበር።
UNHCR በዛሬው መግለጫው ስደተኞች ላይ ያነጣጠሩ “የተሳሰቱ መረጃዎች” መሰራጨታቸውን ቢገልጽም፤ ስለ መረጃዎቹ ምንነት በግልጽ ያለው ነገር የለም።
በጋምቤላ ክልል ባሉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ላይ የቀረበውን ውንጀላ፤ “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ኃላፊዎችም ሆነ ከገለልተኛ አካላት ማጣራት አልቻለችም።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16862/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram