በትግራይ ክልል ህፃፅ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ተጥልለው ከሚገኙ ተፈናቃዮች ውስጥ “ረሃብ” እና “ረሃብ ባስከተለው በሽታ” ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር “ከጊዜ ወደ ጊዜ” እየጨመረ መምጣቱን የተፈናቃዮቹን ጉዳይ የሚከታተሉ አንድ የክልሉ ኃላፊ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።
ህወሓት፣ ስምረት እና ኢሕአፓ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዛሬው ዕለት በየፊናቸው ባወጧቸው መግለጫዎች፤ በህፃፅ ለሚገኙ ተፈናቃዮች አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።
የኤርትራ ስደተኞችን ለማስተናገድ በ2005 ዓ.ም የተቋቋመው ህፃፅ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ፤ በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን፣ አስገደ ወረዳ የሚገኝ ነው።
የስደተኞች መጠለያ ጣቢያው በትግራይ ክልል ጦርነት ወቅት በደረሰበት ጉዳት፤ በውስጡ ተጠልለው የነበሩ ኤርትራውያን ስደተኞች ስፍራውን ጥለው ወደ ሌሎች ቦታዎች ሸሽተዋል።
ለሁለት ዓመት የዘለቀው ደም አፋሳሹ የትግራይ ጦርነት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በተደረገ የግጭት ማቆም ስምምነት በጥቅምት 2015 ዓ.ም. መቆሙን ተከትሎ፤ የህፃፅ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ከምዕራብ ትግራይ ዞን የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን ሲያስተናግድ ቆይቷል።
በህፃፅ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ከ14 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ተጥልለው እንደሚገኙ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የምዕራብ ትግራይ ዞንን እንዲያስተዳድሩ የሾማቸው አቶ ግደይ አዘናው ገልጸዋል።
የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮችን ጉዳይ በቅርበት የሚከታተሉት አቶ ግደይ፤ ከ2015 ዓ.ም. ወዲህ በህፃፅ መጠለያ ጣቢያ “ረሃብ” እና “ረሃብ ባስከተለው በሽታ” ከ330 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
🔴ለዝርዝሩ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16850/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram