በጋምቤላ ክልል ባለፈው ሁለት ሳምንት በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠረ “ግጭት” እና “የጸጥታ መደፍረስ”፤ “የሰዎች ህይወት መጥፋቱን” እና “የአካል ጉዳት መድረሱን” የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።
በክልሉ በሰዎች በህይወት መኖርን ጨምሮ ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳይደርሱ ለመከላከል “በቂ” የጸጥታ አካላት “በአስቸኳይ” እንዲሰማሩ እንዲደረግ ኮሚሽኑ ጠይቋል።
ኢሰመኮ ጥያቄውን ያቀረበው፤ በጋምቤላ የተለያዩ አካባቢዎች “የሚያገረሹ” ግጭቶች በክልሉ ነዋሪዎች ሰብአዊ መብቶች ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት በተመለከተ ዛሬ እሁድ ታህሳስ 12፤ 2018 ባወጣው መግለጫ ነው።
ኮሚሽኑ በዚሁ መግለጫው፤ በክልሉ ውስጥ ባሉት ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ ጋምቤላ ወረዳ እና በጋምቤላ ከተማ ከህዳር 28 ጀምሮ የተፈጠሩ ግጭቶችን እየተከታተለ እንደሚገኝ ገልጿል።
የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ዋና ኢንስፔክተር ኡሞድ ኡጅሉን መገደል ተከትሎ በጋምቤላ ከተማ እና በአካባቢው ባሉት ወረዳዎች እና ቀበሌዎች ግጭት ተፈጥሮ እንደነበር ኢሰመኮ በመግለጫው ጠቅሷል።
የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ባለፈው ማክሰኞ ታህሳስ 7፤ 2018 ከተገደሉ በኋላ በከተማይቱ ለቀናት የቆየ
የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ እንደነበር ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረው ነበር።
ይህንኑ በዛሬው መግለጫው ያረጋገጠው ብሔራዊው የሰብአዊ መብቶች ተቋም፤ በዚህም ሳቢያ “የሰዎችን ህይወት መጥፋቱን” እና “የአካል ጉዳት መድረሱን” አስታውቋል።
ሆኖም ኮሚሽኑ ባለፉት ቀናት በነበሩ ግጭቶች ምን ያህሉ ሰዎች እንደሞቱ እና እንደተጎዱ በመግለጫው ከመዘርዘር ተቆጥቧል።
🔴 ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16845/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram