avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
19.12.2025 15:25
የአሜሪካ የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት ሚኒስትር ክሪስቲ ኖም በተለምዶ “ዲቪ” በመባል በሚታወቀው የፍልሰተኞች “የዳይቨርሲቲ ቪዛ” ፕሮግራም ላይ እገዳ ጣሉ።

ሚኒስትሯ የእገዳ ትዕዛዙን ያስተላለፉት፤ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት መሆኑን ገልጸዋል።

በየዓመቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የሌሎች ሀገራት ሰዎች ወደ አሜሪካ የመግባት እና በሀገሪቱ የመኖር ዕድል የሚያገኙበት ይህ ፕሮግራም እንዲታገድ የተወሰነው፤ ባለፈው ቅዳሜ እና ሰኞ በአሜሪካ ሁለት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ ከተፈጸመው ግድያ ጋር በተገናኘ ነው ተብሏል።

የአሜሪካ ዲፓርትመንት ኦፍ ሆምላንድ ሴኪዩሪቲ ሚኒስትሯ ክሪስቲ ኖም ይህንኑ የሚያስተጋባ መልዕክት ዛሬ በኤክስ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

በብራውን ዩኒቨርስቲ ተኩስ የከፈተው ግለሰብ በዲቪ ፕሮግራም ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መግባቱን በዚሁ መልዕክታቸው የገለጹት ሚኒስትሯ፤ “ይህ ክፉ ግለሰብ ወደ ሀገራችን እንዲገባ በፍጽሙ ሊፈቀድለት አይገባም ነበር” ሲሉ ጽፈዋል።

ሚኒስትሯ በዲቪ ፕሮግራም ምክንያት “አሜሪካውያን ከእንግዲህ በኋላ ጉዳት እንዳይደርስባቸው” ለማረጋገጥ እገዳውን ማስተላለፋቸውን አስታውቀዋል።

ይህ እገዳ ከ55 ሺህ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች በየዓመቱ በአሜሪካ በቋሚነት ለመኖር ዕድል የሚያገኙበትን ፕሮግራም እንዲቆም የሚያደርግ ነው።

በፈረንጆቹ 2025 ወደ 20 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለዲቪ ፕሮግራም አመልክተው እንደነበር የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መረጃ ያመለክታል።

እነዚህ አመልካቾች ውስጥ ልጆቻቸው እና የትዳር አጋሮቻቸው ጋር ተደምረው ዕድለኞች የሆኑ ሰዎች ብዛት 131,060 ነው።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16834/

@EthiopiaInsiderNews
9
👎 6
😁 3
19 7.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram