የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን፤ በአዲሱ የደመወዝ ማስተካከያ ጭማሪ መሰረት “የመስከረም ወር ክፍያ አልተፈጸመልንም” ሲሉ በማህበራቸው አማካኝነት ቅሬታ አቀረቡ።
የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በበኩሉ ችግሩ የተፈጠረው በመረጃ ክፍተት ምክንያት ለፌደራል መንግስት የተላከው የገንዘብ መጠን ጥያቄ ከሚፈለገው በማነሱ እንደሆነ ገልጾ፤ ይህንኑ ለመቅረፍ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታውቋል።
ለመንግስት ሰራተኞች ከመስከረም ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የደመወዝ ማሻሻያ እንደሚደረግ የፌደራል መንግስት ያስታወቀው ባለፈው ዓመት ነሐሴ ነበር።
ሆኖም የደመወዝ ጭማሪው ደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች እስከ ህዳር ወር ተግባራዊ ሳይደረግ ዘግይቷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ በህዳር መጀመሪያ ላይ በሰጠው መግለጫ፤ በአዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ መሰረት የተደረገው ጭማሪ የመስከረም እና የጥቅምት ወር ውዝፍ ክፍያ ከቀናት በኋላ እንደሚፈጸም አስታውቆ ነበር።
የክልሉ መምህራን ማህበር ሰብሳቢ አቶ አማኑኤል ጳውሎስ፤ ቢሮው ይህን መግለጫ ከሰጠ በኋላ የጥቅምት ወር ውዝፍ ክፍያ ለመምህራን ቢፈጸምም የመስከረም ወር ግን በአብዛኛው የክልሉ አካባቢዎች እስካሁን አለመከፈሉን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
ይህን ተከትሎ መምህራን ጥያቄ በማንሳት ላይ መሆናቸውን የገለጹት አቶ አማኑኤል፤ ችግሩ በቀጠለባቸው የክልሉ አካባቢዎች የትምህርት ማቆም አድማ የማድረግ ሙከራዎች እንደነበሩ ገልጸዋል።
በጋሞ እና ኮሬ ዞኖች በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች ተነስቶ ከነበረው የደሞዝ ጭማሪው ክፍያ ጥያቄ ጋራ በተገናኘ፤ ትምህርት ከሳምንት በላይ ተቋርጦ4 መምህራንም ታስረው እንደነበርም አመልክተዋል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16828/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram