avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
17.12.2025 21:03
በጋምቤላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ላይ ግድያ መፈጸሙን ተከትሎ፤ በከተማይቱ ከትላንት ማክሰኞ ረፋድ ጀምሮ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች መቋረጣቸውን ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።

በከተማይቱ የተለያዩ አካባቢዎች ትላንት እና ዛሬ የመሳሪያ ተኩስ እየተሰማ እንደሚገኝም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

ለከተማይቱ አለመረጋጋት መንስኤ የሆነው የጋምቤላ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ኡሞድ ኡጁሉ ግድያ የተፈጸመው ትላንት ማክሰኞ ታህሳስ 7፤ 2018 ከቀኑ አራት ሰዓት ገደማ እንደሆነ የቅርብ ጓደኛቸው ተናግረዋል።

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ኡጉላ ኡጁሉ ግድያውን መፈጸሙን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ቢያረጋግጡም፤ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ግን ተቆጥበዋል።

ከዚህ ክስተት በኋላ በጋምቤላ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች የመሳሪያ ተኩስ እየተሰማ እንደሚገኝም የተገደሉት የፖሊስ አዛዥ የቅርብ ጓደኛ ተናግረዋል።

ግለሰቡ ተኩስ ከሚሰማበት አካባቢ ስላለው ሁኔታ እና ምን አይነት ጉዳት እንደደረሰ ማወቅ እንዳልቻሉ ቢገልጹም፤ ዛሬ ቀትር ላይ ወደ ከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በሄዱበት ወቅት “የሞቱ እና የተጎዱ ሰዎችን” እንደተመለከቱ የአይን እማኝነታቸውን ሰጥተዋል።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው ሁለት የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች፤ ትላንት እና ዛሬ በከተማይቱ የተኩስ እንደሚሰማ እና መደበኛ እንቅስቃሴ መቆሙን አረጋግጠዋል።

በትላንትናው ዕለት የነበረው ተኩስ የቆመው፤ ማታ ሶስት ሰዓት ገደማ ከዘነበው ዝናብ በኋላ እንደነበር አንድ የከተማይቱ ነዋሪ ተናግረዋል።

🔴ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16806/

@EthiopiaInsiderNews
15
😭 1
11 6.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram