የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ከነገ በስቲያ ረቡዕ ታኅሣሥ 8፤ 2018 ዓ.ም ለፌዴሬሽን እና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ንግግር ሊያደርጉ ነው።
ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ የ2 ቀናት የሥራ ጉብኝት የሚያካሄዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ፤ ንግግር የሚያደርጉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሚገኙበት የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መድረክ ላይ ነው።
የፌደሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ለአባላቱ በላከው “አስቸኳይ” መልዕክት፥ “የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ለሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ መድረክ ንግግር እንደሚያደርጉ” አስታውቋል።
ምክር ቤቱ በዚሁ መልዕክቱ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በከተማው ዙሪያ የሚኖሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ከነገ በስቲያ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ እንዲገኙ አሳስቧል።
“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነጋገረቻቸው አንድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል ይሄው መልዕክት እንደደረሳቸው አረጋግጠዋል።
የረቡዕውን የጋራ መድረክ በተመለከተ ለገዢው ፓርቲ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተመሳሳይ መልዕክት ቢላክም፤ የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ ተወካዮች ስለ ጉዳዩ በቀጥታ መረጃ እንዳልደረሳቸው ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
የነገ በስቲያው የጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ የፓርላማ ንግግር ዋነኛ ትኩረት ምን እንደሆነ ለምክር ቤት አባላቱ የተባለ ነገር የለም።
የህንዱ ኤንዲቲቪ ቴሌቪዥን ጣቢያ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የዲሞክራሲ እናት” ባሏት በሀገራቸው ህንድ ጉዞ ላይ በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ላይ ሀሳባቸውን ለማካፈል “በጉጉት እንደሚጠባበቁ” መግለጻቸውን ዘግቧል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2025/16789/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram