avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
14.12.2025 18:16
የአሜሪካዊቷ ሚኒስትር ክሪስቲ ኖም ውሳኔ በቦስተን ከተማ ለምትኖረው ኢትዮጵያዊቷ ነርስ *ሜላት ገብረ እግዚያብሔር “መርዶ” ሆኖባታል።

የአሜሪካ ዲፓርትመንት ኦፍ ሆምላንድ ሴኪዩሪቲ (Department of Homeland Security) ሚኒስትር የሆኑት ክሪስቲ ከትላንት በስቲያ አርብ ያስተላለፉት ውሳኔ፤ እንደ እርሷ ሁሉ “ጊዜያዊ ከለላ” አግኝተው በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን አስደንግጧል።
 
የ54 ዓመቷ ሚኒስትር የአርብ ዕለት ውሳኔ፤ ሜላትን ጨምሮ በሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ለመቆየት የሚያስችላቸውን ሕጋዊ ከለላ ያሳጣ ነው። ውሳኔው ይፋ ከተደረገ በኋላ ከ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ጋር አጭር ቆይታ የነበራት ሜላት “እንዴት እንደምተኛም አላውቅም” ስትል ጭንቀቷን አጋርታለች።

ሜላትን ለጭንቀት እና ፍርሃት የዳረጋት ውሳኔ የተላለፈው፤ በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ያለው ሁኔታ “ጊዜያዊ ከለላ” ለመስጠት የሚያስፈልገውን “ቅድመ ሁኔታ” እንደ ቀደሙት ጊዜያት “የሚያሟላ አይደለም” በሚል ምክንያት ነው። በአሜሪካ ለተወሰነ ጊዜ መቆየት የሚያስችለውን “ጊዜያዊ ከለላ” የሚያገኙት፤ ግጭት እየተካሄደባቸው ከሚገኙ፣ የተፈጥሮ አደጋ ወይም ሌሎች ፖለቲካዊ ቀውሶች ከገጠማቸው ሀገራት ለሚጓዙ ዜጎች ነው።

ከለላው የተሰጣቸው ሰዎች ወደ ትውልድ ሀገራቸው በግዳጅ ከመመለስ በህግ የሚጠበቁ ሲሆን በአሜሪካ ለመስራት የሚያስችላቸው ፈቃድ ያገኛሉ። ኢትዮጵያውያን ይህን የሰብአዊ ጥበቃ ያገኙት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ወቅት በታህሳስ 2015 ዓ.ም ነበር።

በወቅቱ ከለላውን ለማግኘት ብቁ የሆኑ 26,700 ኢትዮጵያውያን በአሜሪካ ይገኛሉ ተብሎ ይገመት ነበር።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16779/

@EthiopiaInsiderNews
18
😁 3
🤯 1
6 8.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram