avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
11.12.2025 19:48
ብሔራዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጋምቤላ ክልል በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ግጭቶች አሳሳቢ መሆናቸውን በተለያየ ጊዜ በሚያወጣቸው መግለጫዎች እና ሪፖርቶች ሲገልጽ ቆይቷል። የኮሚሽኑ የሥራ ኃላፊዎች ከሦስት ሳምንት በፊት በክልሉ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት፤ ይኸው ጉዳይ ተነስቶ ነበር።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጋር አለሚቱ ኡሙድ እና ከሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር በነበራቸው ውይይት፤ በክልሉ “አልፎ አልፎ” ይከሰታሉ ያሏቸው “ግጭቶች” እና “ጥቃቶችን” ለማስቀረት፤ “ጠንካራ የቅድመ መከላከል ሥራ እንዲሠራ” ጠይቀው ነበር። ኮሚሽነሩ ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በክልሉ ዳግም በተፈጸመ ጥቃት ሳቢያ በጋምቤላ ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሏል።

የክልሉ መንግስት መቀመጫ በሆነችው የጋምቤላ ከተማ ከምሽት አንድ ሰዓት በኋላ በሚደረግ የተሽከርካሪ እና የሰው እንቅስቃሴ ላይ ክልከላ የተጣለው ከትላንት በስቲያ ማክሰኞ ህዳር 30፤ 2018 ነው።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” በትላንትናው ዕለት ያነጋገረቻቸው አንድ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪ፤ በከተማይቱ ባለው የጸጥታ መደፍረስ ምክንያት እርሳቸው በሚገኙበት አካባቢ ትምህርት ቤቶች እና ባንኮች ዝግ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የመንግስት ሰራተኛ የሆኑት ሌላኛዋ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪ ግን በትላንትናው ዕለት በሥራ ገበታቸው ላይ እንዳልተገኙ እና ልጆቻቸውን ዛሬም ጭምር ወደ ትምህርት ቤት እንዳልላኩ ተናግረዋል። በዛሬው ዕለት የተወሰነ የሰዎች እንቅስቃሴ ቢኖርም በአቅራቢያቸው የሚገኝ ባንክ አሁንም ዝግ እንደሆነ ገልጸዋል።

🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16775/

@EthiopiaInsiderNews
14
🤔 9
10 9.7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram