ምስላዊ መረጃ፦ ዛሬ ማክሰኞ ህዳር 30፤ 2018 ይፋ የተደረገው የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ፤ በረቂቅ ደረጃ ከነበረው የጊዜ ሽግሽግ ተደርጎበታል። ምርጫ ቦርድ የመጪውን ጠቅላላ ምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ አዘጋጅቶ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲወያዩበት ያቀረበው ጥቅምት 10፤ 2018 ነበር።
ቦርዱ በዚሁ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ከመገናኛ ብዙሃን ተወካዮች ጋር በጥቅምት ወር አጋማሽ ተመሳሳይ ውይይት ማድረጉም አይዘነጋም። ምርጫ ቦርድ ይህንኑ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ በመጠቀም የቅድመ ምርጫ ዝግጅቶችን ሲያከናውን ቢቆይም፤ እስከ ዛሬ ድረስ ይፋዊ የምርጫ ሂደት ዝርዝሮችን ሳያሳውቅ ቆይቷል።
በይፋዊ የጊዜ ሰሌዳው ላይ የተዘረዘሩ አንኳር የምርጫ ሂደት ክንውኖችን ከታች ከተያያዘው ምስላዊ መረጃ ላይ ይመልከቱ። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram