avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
09.12.2025 12:59
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ሰኞ ግንቦት 24፤ 2018 ሆኖ መጽደቁን አስታወቀ። ቦርዱ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን ይፋ ባደረገው የጸደቀ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ፤ የምርጫ ውጤት በቦርዱ ደረጃ ይፋ የሚደረገው ሰኔ 4 ቀን እንደሆነ ገልጿል።

በምርጫ የጊዜ ሰሌዳው መሰረት በመጪው ምርጫ የሚወዳደሩ ዕጩዎች ምዝገባው የሚከናወነው ከጥር 1 እስከ የካቲት 1 ባለው አንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይሆናል። የምርጫ ተወዳዳሪዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ የሚያደርጉበት ጊዜ ከጥር 1 ጀምሮ እስከ ግንቦት 19 እንደሚቆይም በጊዜ ሰሌዳው ላይ ሰፍሯል።

እንደ ዕጩዎች ምዝገባ ሁሉ አንድ ወር ጊዜ የተሰጠው የመራጮች ምዝገባ የሚካሄደው ከየካቲት 7 እስከ መጋቢት 7 እንደሆነ ምርጫ ቦርድ አመልክቷል። በቴክኖሎጂ በመታገዝ ራሳቸውን ለሚመዘግቡ (self registration) መራጮች በአንጻሩ 2 ወር የተጠጋ ጊዜ ተመድቦላቸዋል። በዚህ ሂደት የሚሳተፉ መራጮች የሚመዘገቡት ከጥር 15 እስከ መጋቢት 7 ባለው ጊዜ ውስጥ ነው።

መራጮች ሰኞ ግንቦት 24 ድምጻቸው ከሰጡ በኋላ ውጤቱን በምርጫ ጣቢያ ደረጃ በማግስቱ መመልከት እንደሚችሉ በጊዜ ሰሌዳው ላይ ተመልክቷል። በምርጫ ክልል ደረጃ ጊዜያዊ ውጤት የሚገለጸው፤ ከድምጽ መስጪያው ማግስት ጀምሮ እስከ ግንቦት 29 ድረስ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት እንደሆነ በጊዜ ሰሌዳው ላይ ተቀምጧል።

የምርጫ ክልሎች ውጤቶችን ለምርጫ ቦርድ የሚያስረክቡት ከግንቦት 26 እስከ ሰኔ 1 ድረስ ባሉት ጊዜያት እንደሚሆንም በይፋዊ የጊዜ ሰሌዳው ላይ ተገልጿል። ምርጫ ቦርድ ውጤቶችን የማረጋገጥ ስራዎችን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 2 ባሉት ቀናት ካከናወነ በኋላ ይፋዊ የምርጫ ውጤቱን ሐሙስ ሰኔ 4 ይገልጻል ተብሎ ይጠበቃል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@EthiopiaInsiderNews
😁 13
5
👎 1
🥰 1
😭 1
12 9.5K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram