avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
28.11.2025 18:28
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች “ገቢ ለመሰብሰብ” በሚል የተዘረጉ ኬላዎች “በፍጥነት እንዲነሱ” የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ትዕዛዝ ሰጠ።

ይህን ትዕዛዝ ተላልፎ በተገኘ ማንኛውም የመንግስት አካል ላይ የጸጥታ ኃይሎች ለሚወስዱት “እርምጃ” ቢሮው ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑንም አስታውቋል። 

ቢሮው ይህንን ያሳወቀው፤ በክልሉ የዞን እና የከተማ አስተዳደር ስር ላሉ የገቢዎች መምሪያዎች ከትላንት በስቲያ ረቡዕ ህዳር 17፤ 2018 በጻፈው ደብዳቤ ነው።

መስሪያ ቤቱ ትዕዛዙን ለመምሪያዎቹ ያስተላለፈው፤ የአማራ ክልልን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች “ገትተዋል” የተባሉ ኬላዎች እንዲነሱ ከክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ደብዳቤ ከተጻፈለት ከአንድ ሳምንት ገደማ በኋላ ነው።
 
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የተቋቋሙ ኬላዎች የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርት እንቅስቃሴን “ሲያስተጓጉሉ” እና “ሲያዘገዩ” እንደነበር በደብዳቤው የጠቀሰው የክልሉ ገቢዎች ቢሮ፤ “ያልተገባ ክፍያ በማስከፈል” የምርት ዋጋ እንዲጨምር ማድረጋቸውን አትቷል። እነዚህ ድርጊቶች “የኑሮ ውድነትን በማባባስ”፤ በሸማቾች ላይ ጫና ማሳደራቸውንም ደብዳቤው አክሏል።

በአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የከተማ አገልግሎት ገቢ ባለሙያ የሆኑት አቶ አሰፋ ወርቅዬ፤ ዞኖች እና ከተሞች ኬላዎችን ሲያቋቋሙ የነበረው “ገቢን ለመሰብሰብ በሚደረግ ጥረት” እንደነበር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስረድተዋል።

ሆኖም በተወሰኑ ኪሎሜትሮች ልዩነት የሚቋቋሙ ኬላዎች መበራከታቸው የአሽከርካሪዎች “መጉላላት” ማስከተሉን እንዲሁም በእነዚህ ቦታዎች የሚጠየቁ ክፍያዎች “የምርት ዋጋ ጭማሪ እንዲኖር ማድረጉን” አብራርተዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16755/

@EthiopiaInsiderNews
26
👍 8
😁 2
10 11K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram